ሴቶች ሠላምን በመገንባት ረገድ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው – ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴቶች በመፍትሄ አመንጪነት ሰላም እንዲሰፍን ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡
ሴቶች ተጠቂዎች ብቻ ሳይሆኑ÷ በመፍትሄ አመንጪነት ግጭት እንዳይከሰት አስቀድሞ በመከላከል፣ በሰላማዊ ድርድር፣ በሽምግልና እና ከታችኛው እርከን ጀምሮ ሠላምን በመገንባት ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ፡፡
ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ይህን ያሉት÷ የአፍሪካ ሴቶች መሪዎች ኔትወርክ በበይነ መረብ ባካሄደው 3ኛው የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን የሴቶች መሪዎች ፎረም ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር መሆኑን ከፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡