Fana: At a Speed of Life!

በግብርናው ዘርፍ የሚካሄደው ጥረት ዓላማ ድህነትን አሸንፎ ታሪክ መስራት ነው – አቶ ኡስማን ሱሩር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርናው ዘርፍ እየተካሄደ ያለው ጥረት በግንባር የሚካሄደው ጦርነት አካል መሆኑንና ዋነኛ ዓላማውም ድህነትን አሸንፎ ታሪክ መስራት ነው ሲሉ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡስማን ሱሩር ገለጹ።
በግብርናው ዘርፍ ውጤት ለማምጣት ከበጋ መስኖ በተጨማሪ ሰብልን በአግባቡ ለመሰብሰብ በትኩረት እተሰራ ነው ያሉት የዞኑ ምክትል አስተዳደሪና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ ናቸው፡፡
ምርት እንዳይባክን 45 ኮምባይነሮች በየቀበሌው ተሰማርተው እየሰበሰቡ እንደሆነ የግብርና መምሪያ ሀላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
የልማት አርበኞችም÷ በበጋ በመስኖ ልማት ያዘጋጀነው መሬት ውጤታማ እንዲሆን በቂ የሞተር ስርጭት ያስፈልገናል ብለዋል።
ለበጋ መስኖ እያደረጉት ያለው ትግል በግንባር ከሚደረገው ትግል አይተናነስምና ዝግጅቱን አጠናክሮ መቀጠልና በበጋ የስንዴ ባለቤት መሆን ግዴታ ነው ያሉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ናቸው፡፡
ምርት ሲሰበሰብ እንዳይባክን በቂ ዘመናዊ ማሽን ወደ ስራ መግባቱን እና በክልሉ በበጋ መስኖ 15 ሺህ ሄክታር ለማልማት እቅድ የተያዘ ሲሆን÷ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ይሰበሰባል ተብሏል።
በጥላሁን ይልማ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.