የጋምቤላ ክልል በአፋርና በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ ሊያደርግ ነዉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል መንግስት በአፋር እና በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ።
የክልሉ ህዝብና መንግስት ለአገር መከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚያደረገዉን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ተናግረዋል።
የጋምቤላ ክልል ህዝብና መንግስት ለህልዉና ዘመቻዉ በግንባር እየተዋደቁ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በህወሓት የሽብር ቡድን ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ ወገኖች የማያቋርጥ ድጋፍ ያደርጋልም ነዉ ያሉት።
ህወሓት በወረራቸዉ የአማራና የአፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች 4 ሚሊየን ብር የክልሉ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን ገልፀዉ በቅርቡ ለተጎጂዎቹ እንደሚደርስ ገልፀዋል።
በሰሜኑ የአገሪቱ አካባቢዎች እየተካሄደ ካለዉ የህልዉና ዘመቻ ባልተናነሰ በመተከል ዞን የህወሓት ተላላኪ ቡድን ለመደምሰስ ለተሰማራዉ የክልሉ ልዩ ሃይል 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉንም አብራርተዋል።
መከላከያ ሰራዊቱንና በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉና የተጎዱ ወገኖችን በገንዘብም ሆነ በዓይነት የመደገፉ ስራ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዉ÷ እስካሁን ከ27 ሚሊየን ብር በላይ በክልሉ ከሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች፣ አመራሮች እና ከህብረተሰቡ በማሰባሰብ ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ተልኳል ማለታቸዉን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!