Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ  ለኢትዮጵያ አፍራሾች እንደ እግር እሳት ሆናለች-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ  ለኢትዮጵያ አፍራሾች እንደ እግር እሳት ሆናለች ሲሉ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ፥ አዲስ አበባ ለጠላቶቿ የማትቀመስ የህልም እንጀራ ፤ ለወዳጆቿ ዞሮ መግቢያ የሆነች  የኢትዮጵያዊያንና አፍሪካዊያን ምቹ ቤት ናት  ብለዋል።

ሊያቃጥሏት የተመኙ ጠላቶቿ  ሺህ ጊዜ ቢመኟት እንደ ሰማይ እርቃባቸዋለች ፤ እንደ እግር እሳት መቆሚያ መቀመጫ አሳጥታቸዋለች ሲሉ ገልጸዋል ።

መቼም ይህ የእብደት ከንቱ ህልማቸው አይሳካም ፤ በገቡበት ይቀበራሉና ብለዋል  ።

በመዲናችን አዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢያቸውን ሁለንተናዊ ሰላምና ፀጥታ የሚያስጠብቁ  የተለያዩ  ህዝባዊ አደረጃጀቶችን በመፍጠር በቂ ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ወደ ተልዕኮ እንዲገቡ ተደርጓልም ነው ያሉት ።

በዚህ ሕዝባዊ የፀጥታ አደረጃጀት በአጭር ጊዜ ዉስጥ ተጨባጭ ለዉጥ ማምጣት የተቻለ ሲሆን፥ የተለያዩ አይነት የንጥቂያና የሌብነት ወንጀሎችም ቀንሰዋል ፤ የተለያዩ በህቡዕ የተደራጁ የጥፋትና የሽብር ሀይሎች መፈናፈኛ አጥተዋል ፤ ሰርጎ ገቦችም እየተመነጠሩ ይገኛሉ ።

ነገሩ ሁሉ ” ላም አለኝ በሰማይ “የሆነባቸው የጁንታዉ ህወሃት ፤ ሸኔ እና የታሪካዊ  ጠላቶቻችን ተላላኪዎች ሁሉ መፈናፈኛ አጥተዋል ፤ያከማቹትን የጦር መሳሪያ ሳይቀር በየጥጋ ጥጉና የቆሻሻ መጣያ ገንዳዎች አካባቢ እየጣሉ ይገኛሉ ብለዋል ከንቲባዋ ።

አዲስአበባ አሁንም ሙሉ ትኩረቷን ጀግኖችን በማጀገን እና የመዲናችንን ሰላምና ደህንነትን በአስተማማኝ ደረጃ ማስጠበቅ ላይ ከፍተኛ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ነውም  ሲሉ ገልጸዋል

ለዚህም ወደ ስራ እየገቡ ያሉ ህዝባዊ አደረጃጀቶች ከሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት አስተማማኝ ሰላም እያረጋገጡ መጓዛቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.