Fana: At a Speed of Life!

በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢ የሚገኙ ህዝቦችን አብሮነት ለማጠናከር እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የሚገኙ ህዝቦችን አብሮነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን የክልሎቹ ሰላም ግንባታ እና ፀጥታ ቢሮዎች አስታወቁ። በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች ባለው የሰላም ሁኔታ…

ቱርክ ከኢትጵያ ጋር ያላት ሁለንተናዊ የዲፕሎማሲ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ-ቱርክ ታሪካዊ ወዳጅነት በሁለንተናዊ የዲፕሎማሲ ትብብር መስኮች ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር በርክ ባራን ገለጹ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮ-ቱርክ ወዳጅነት…

የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሰራባ ተሐድሶ ማሰልጠኛ ማዕከል አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ አም ሲ) የመንግሥትንና የሕዝብን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሰራባ ተሐድሶ ማሰልጠኛ ማዕከል አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ታጣቂዎቹ የክልሉ ሕዝብ በዚህ ግጭት ያተረፈው ሞትና ውድመት መሆኑን በመረዳታቸው የሰላም ጥሪውን መቀበላቸውን ተናግረው፤…

ዩክሬን ወደ አውሮፓ ሀገራት የሚተላለፈውን የሩሲያ ጋዝ አቋረጠች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዩክሬን በኩል ለአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሚቀርበው የሩሲያ ጋዝ በዩክሬን የጋዝ ማመላለሻ ኦፕሬተር ናፍቶጋዝና በሩሲያ ጋዝፕሮም መካከል ያለው የአምስት ዓመት ስምምነት ማብቃቱ ተሰምቷል፡፡ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ፥ በመሬታችን…

የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ የመቅረብ ቅድመ ሁኔታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ በሚገኙ ባንኮች የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ ዛሬ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል፡፡ ቅድመ ሁኔታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት ነው ከዛሬ…

አሜሪካ ለዩክሬን 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ለመደገፍ ቃል ገባች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ልታደርግ ነው፡፡ ድጋፉዩክሬን ከሩሲያ ከሚሰነዘርባት ጥቃት ራሷን እንድትከላከል ያግዛታል ተብሏል፡፡ በፈረንጆቹ ጥር 20 ቀን 2025 ከነጩ ቤተመንግስት የሚወጡት…

የአውሮፕላን አደጋ መደጋገምና የአቪየሽን ኢንዱስትሪው …

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰው ልጅ መሻት ከኖረበት ቤት፣ መንደር፣ ሀገር እና ዓለም ብቻ ሊገደብ አለመቻሉን በየጊዜው ከሰማይ ረቅቆ የእንግዳ ፕላኔቶችን አድማስ ሲበረብር መታየቱ ማረጋገጫ ነው፡፡ ዓለምን ከሚያስደንቅ የሰው ልጅ ስኬቶች መካከል የሚጠቀሰው አውሮፕላን…

በጌድዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የተመራ ልዑክ የዶራሌ ሁለገብ ወደብና ተርሚናልን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የተመራ ልዑክ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ እና ተርሚናል ተገኝቶ አጠቃላይ የገቢ-ወጪ ምርት ሂደት ጎብኝቷል። ልዑኩ በጉብኝቱ ወቅት ከወደብ የስራ ኃላፊዎች ጋር ስለ2017/18 የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን…

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለመደራደር ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለመደራደር ቅድመ ሁኔታዎቿን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባት አስታውቃለች፡፡ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያለውን ግጭት በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ…

የቤተ-መንግሥት ሙዚየም ለጉብኝት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤተ-መንግሥት ሙዚየም ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የታላቁ ቤተ-መንግሥት እድሳት የታሪክ እና የባሕል ቅርሳችንን ጠብቆ ለማቆየት የምናደርገው ጥረት ከፍ ያለ ርምጃ ነው ሲል ጽሕፈት ቤቱ በማኅበራዊ…