Fana: At a Speed of Life!

ለመጀመሪያው ዙር የሐጅ ተጓዦች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘንድሮው 1 ሺህ 445ኛው የሐጅ ሥነ-ሥርዓት የመጀመሪያ ዙር ተጓዦች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሽኝት ተደረገ። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራርና…

የኢትዮጵያና ሳዑዲን ወታደራዊ ትብብር ለማሳደግ ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ ዓረቢያን ወታደራዊ መረጃና ደኅንነት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ ውይይት በሳዑዲ ዓረቢያ ተካሂዷል፡፡ በመከላከያ ሠራዊት የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና የተመራ ከፍተኛ የወታደራዊ ልዑክ…

ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ድጋፍ ይደረጋል- አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቶች ተደራጅተው ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡ ርዕሰ መሥተዳድሩ በወላይታ ዞን ዱጉና ፋንጎ ወረዳ በአርሶ አደሮችና በወጣቶች በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኝን…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 1 ሺህ 445ኛውን የሐጅ ጉዞ በስኬት ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 1 ሺህ 445ኛውን የሐጅ ጉዞ በስኬት ለማካሄድ የሚያስችለውን ልዩ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ ይህ ልዩ ዝግጅት ለተከታታይ ዓመታት የተደረገ መሆኑንየአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ተጠሪ ተቋማት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ ተቋማት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ግምገማ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት እየተካሄደ ነው። በግምገማው ተጠሪ ተቋማት ሀገራዊ የልማትና የለውጥ ኢኒሼቲቮችን ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ በሚሆን መልኩ…

ማንቼስተር ሲቲ የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ሲቲ ብርቱ ፉክክር በታየበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን ባገኘው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ዌስትሃምን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ 3 ለ1 ማሸነፉን ተከትሎ…

ኢትዮጵያ በአኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ጠንካራ ተሳትፎ ለማድረግ እየተዘጋጀች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ጠንካራ ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝግጅቶችን እያደረገች መሆኗን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ከአኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ጋር በተገናኘ የጉሙሩክ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ ዘመናዊ አሠራር እየተዘረጋ…

በጤናው ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤናማ እና አምራች ማኅበረሰብ ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለጹ፡፡ አቶ አሻድሊ በአሶሳ ዞን መንጌ ወረዳ ከ40 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ ለሚገነባው የካሻፍ…

ኢትዮጵያ 3ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍ የቡድኑ አባል የነበሩት ኃ/ማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ1954 ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋች የነበሩት ኃይለማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ በቅፅል ስማቸው "ሻሾ" በሚል በስፖርት ቤተሰቡ በስፋት የሚታወቁት ኃይለማርያም መኮንን÷ ከ1940ዎቹ መጨረሻ…

ቄስ በላይ መኮንንን ጨምሮ በ5 ግለሰቦች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቄስ በላይ መኮንንን ጨምሮ በአምስት ግለሰቦች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ በመደበኛ ችሎት ተመሰረተባቸው። ክሱ የተመሰረተባቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን÷ ተከሳሾቹም 1ኛ ቄስ በላይ…