Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ለጤናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የማይበገር የጤና ሥርዓትን እውን ለማድረግ እና ሁለንተናዊ የጤና ሽፋንን በማሻሻል ረገድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከኮሚሽኑ ልዑክ ጋር በትብብር በሚሠሩ…

ኅብረተሰቡ የፕላስቲክ ቆሻሻን ለይቶ ለማኅበራት በመስጠት ብክለትን ለመከላከል የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኅብረተሰቡ የፕላስቲክ ቆሻሻን ለይቶ ለተደራጁ ማኅበራት በመስጠት የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የተጀመረውን ዘመቻ እንዲያግዝ የሲዳማ ክልል ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ጥሪ አቀረበ፡፡ "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ሐሳብ ክልል…

15ኛው የአፋር ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 15ኛው የአፋር ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ አዲስ አበባ ገቡ። የሱልጣን አሊሚራህ ልጅ የሆኑት 15ኛው የአፋር ሱልጣን አሕመድ የመላው አፋር ሱልጣን የነበሩት ወንድማቸው ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ ማረፋቸውን ተከትሎ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር መሾማቸው…

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ 28 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለውጭ ገበያ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ28 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡ በሌላ በኩል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ850 ለሚልቁ ወገኖች አዲስ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ…

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሳው እሳት እንዳይዛመት መከላከል ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሳውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር በተደረገ ርብርብ እሳቱ እንዳይዛመት መከላከል መቻሉን የፓርኩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ በፓርኩ ክልል ውስጥ አምባራስ ቀበሌ ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የተነሳው እሳት በጓሳ…

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ማንቼስተር ሲቲ ለዋንጫ ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ እና ማንቼስተር ሲቲ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ፡፡ ማንቼስተር ዩናይትድና ኮቬንትሪ ሲቲ ዛሬ ያደረጉት ጨዋታ መደበኛና በጭማሪ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3 አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡…

ሊቨርፑል ፉልሃምን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፉልሃምን የገጠመው ሊቨርፑል 3ለ 1 አሸንፏል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው አጋማሽ አንድ አቻ ሆነው ወደ መልበሻ ክፍል ቢያመሩም ከዕረፍት መልስ ሊቨርፑል ባስቆጠራቸው 2 ጎሎች ፉልሃም ሽንፈት አስተናግዷል፡፡…

ኤቨርተን፣ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄዱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ኤቨርተን፣ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ በዚህም ኤቨርተን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ክሪስታል ፓላስ ዌስትሃምን 5 ለ 2 ረትቷል፡፡ እንዲሁም…

ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን ጎል አማኑኤል አድማሱ በጨዋታ ሲያስቆጥር የመቻልን ጎል ደግሞ ምንይሉ ወንድሙ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡

ያለአግባብ ከተወሰደው ብር 96 ነጥብ 3 በመቶው ተመልሷል – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው የብር መጠን 96 ነጥብ 3 በመቶው መመለሱን አስታውቋል፡፡ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ባጋጠመ ችግር ምክንያት 801 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ያለአግባብ መወሰዱን…