Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ወንጀለኛ የነበሩ 178 የሠራዊት አባላት ይቅርታ ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 206 (ኤፍ ቢ ሲ) ወንጀለኛ በመሆናቸው እስከ ሞት ፍርድ ተወስኖባቸው ለነበሩ 178 የሠራዊት አባላት በአዲስ ዓመት ይቅርታ መደረጉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ከነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ አንዳንድ የሠራዊት አባላት የተሰጣቸውን…

ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ጋር በመሆን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ዕቃ መያዙን ነው…

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለ468 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ468 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርገዋል፡፡ ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 463ቱ በሙሉ ይቅርታ ከእስር እንዲለቀቁ መወሰኑን የርዕሰ…

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ለአሽከርካሪዎችና ተጓዦች የመልካም በዓል መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በትራንስፖርት ተርሚናሎች ተገኝተው ለአሽከርካሪዎችና ተጓዦች “እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሳችሁ” የመልካም በዓል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ሚኒስትሩ በላምበረትና አዲስ ከተማ (አውቶቢስ…

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለ150 አይነ ስውራን ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል፡፡ ቀዳማዊት እመቤቷ የአዲስ ዓመት በዓልን በማስመልከት ነው በርጠሚዎስ ክርስቲያናዊ ማህበር ድጋፍ ለሚያደርግላቸው 150 አይነ ስውራን ወገኖች ማዕድ ያጋሩት፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለ892 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ892 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ፡፡ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ እንደገለጹት÷ ይቅርታ የተደረገላቸው የሕግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩ እና…

እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል ከኢትዮጵያጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጻለች፡፡ በውጪ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ በተዘጋጀው ውይይት ላይ አዲስ የተሾሙት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደርና የፖርላማ ልዑካን ተሳትፈዋል።…

404 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 404 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡…

አምባሳደር ታዬ ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበርን (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም÷በቀጣናው ዘላቂ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲኖር በአውሮፓ ህብረት እና ባለድርሻ አካላት…

የአዋሬ መንደር ለዜጎች ምቹ ሀገር የመገንባትና አካታች ልማትን እውን የማድረግ ምሳሌ ነው -ሚኒስትሮች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዋሬ መንደር ላይ የታየው ለውጥ ለዜጎች ምቹ ሀገር የመገንባትና አካታች ልማትን እውን የማድረግ ምሳሌ መሆኑን ሚኒስትሮች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከቀናት በፊት በአዋሬ መንደር የተገነቡ…