Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ለሀገራዊ የዕድገት ጉዞ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ወሳኝ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀገራችን የዕድገት ጉዞ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ወሳኝ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ፡፡ የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ዛሬ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄዱን አቶ ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር…

የመዲናዋ ነዋሪዎች በነገው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በነገው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በነቂስ በመውጣት አረንጓዴ ዐሻራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ ቀረበ፡፡ የአሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ “ውድ…

ሲፍ ፋውንዴሽን በጤናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አንደሚያጠናክር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከሕጻናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (ሲፍ) ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኬት ሃምፕተን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ሲፍ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ሐሩራማ በሽታዎችን ጨምሮ በስርዓተ ምግብና መከላከል በሚቻል ምክንያት የሚመጣ ሞትን…

የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ እየተወያዩ ነው፡፡ በውይይቱ የክልሉ ም/ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ የሰሜን ምሥራቅ እዝ ዋና አዛዣ ጄኔራል አሰፋ ቸኮልና በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ…

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ እየተሠራ ነው – ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የቅድመ መከላከል ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በሰጡት መግለጫ÷ የዝንጅሮ ፈንጣጣ በሽታ በዓለም የጤና ድርጅት የሕብረተሰብ ጤና ስጋት…

አቶ አረጋ ከበደ የክልሉ ህዝብ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ህዝብ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ዓሻራውን የማኖር ተግባር አካል እንዲሆን  የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር  አረጋ ከበደ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ርእሰ መሥተዳድሩ በነገው ዕለት ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር…

የሀገርን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራት ይገባል- ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ በገበያ መር፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ የበቃና የሰለጠነ የሰው ሃይል የማፍራት ጉዳይ ወሳኝ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተለያዩ…

በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል የተያዘው ቁርጠኝነት የሚደነቅ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ያሳየችው ቁርጠኝነት የሚደነቅ መሆኑን ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ባለሙያዎች ገለጹ። ኢትዮጵያ ነገ በምታከናውነው የአንድ ጀምበር…

አቶ አወል የክልሉ ህዝብ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ህዝብ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በንቃት እንዲሳተፍ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ርዕሰ መሥተዳድሩ በክልሉ ለሚከናወነው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የቅድመ ዝግጅት…

ሩሲያውያን ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ ይታገሱ (ዶ/ር) በሩሲያ ሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል…