Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ሰላም በተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል – ቢሮው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ሰላም በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ገለጸ። በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው በወቅታዊ የክልሉ የሰላም…

ግድቡ የኔ ነው’ የሚለው አባባል በኢትዮጵያውያን ላይ ትልቅ የባለቤትነት ስሜት ፈጥሯል – አምባሳደር ስለሺ በቀለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ግድቡ የኔ ነው’ የሚለው አባባል ኢትዮጵያውያን በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ትልቅ የባለቤትነትና የተነሳሽነት ስሜትን እንዲፈጠርባቸው አድርጓል ሲሉ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርና የግድቡ ዋና ተደራዳሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር)…

ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝን ተግባራዊ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓትን በዛሬው እለት በይፋ አስጀምሯል። የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ፕሮግራሙን በይፋ ሲያስጀምሩ የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኃላፊዎች…

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የ10 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ የግብርና ወጪ ምርትን ለማበረታታት የሚያስችል የ10 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት አድርገዋል፡፡ ደቡብ ኮሪያ በኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) አማካኝነት ያደረገችው ድጋፍ…

በጋምቤላ ክልል አንድነትን ለማሻከር የሚሠሩትን በማጋለጥ ሕብረተሰቡ ትብብሩን እንዲያጠናክር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የሕዝብን አንድነት ለማሻከር የሚሠሩ ጽንፈኛ ኃይሎችን አጋልጦ ለመንግሥት በመስጠት ረገድ ሕብረተሰቡ ትብብሩን እንዲያጠናክር የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ። የኮሚሽኑ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል…

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ከሆኑት ጄን ቻርልስ ካራምባን ጋር ተወያዩ፡፡ በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ ጉዳዮች እና ከአሁን በፊት ሁለቱ ሀገራት በትብብር የሚሰሩባቸውን ጉዳዮች ይበልጥ…

አማራ ባንክ ከኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ የ90 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር አክሲዮን ገዛ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ባንክ ከኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ የ90 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የአክሲዮን ግዥ ፈጽሟል። የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጫንያለው ደምሴ÷ አማራ ባንክ ከባንክ ባሻገር ብሎ ሲነሳ በልዩ ልዩ ዘርፎች ተሳትፎ እንደሚያደርግ ለመግለጽ ነው፤…

50 የእጅ ቦምብ ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊያቀብሉ ነበር ተብለው የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 50 የእጅ ቦምብ ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊያቀብሉ ነበር ተብለው የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች ላይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ህገመንግስታዊና በህገመንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጠ።…

ፓርቲው ያጋጠሙትን ፈተናዎችና ጫናዎች በፅናት በማለፍ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድል እያስመዘገበ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ያጋጠሙትን ፈተናዎችና ጫናዎች በፅናት በማለፍ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድል እያስመዘገበ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። ''ቃል በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና'' በሚል መሪ ሃሳብ በኦሮሚያ…

ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ በደቡብ ሱዳን ለሚሰማሩ ከፍተኛ መኮንኖች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ በደቡብ ሱዳን ለሚሰማሩ የኢትዮጵያ ፖሊስ ከፍተኛ መኮንኖች ሽኝት ተደርጓል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት÷የኢትዮጵያ ፖሊስ ሠራዊት በሥነ-ምግባሩ እና…