Browsing Category
የሀገር ውስጥ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሱዳን ሪፐብሊክ ሉዓላዊ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሱዳን ሪፐብሊክ ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልቡርሃን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የጋራ በሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡…
ሠራዊቱ በሶማሌ ክልል በጎርፍ ለተጠቁ የህብረተሠብ ክፍሎች የምግብ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በሊበን ዞን በዶሎ አዶ እና በአካባቢው በሚገኙ ወረዳዎች በጎርፍ ለተጠቁ የህብረተሠብ ክፍሎች የመከላከያ ሠራዊት የደረቅ ምግብ ድጋፍ አደረገ።
በስፍራው ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው ኮር ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ኮሎኔል አየለ…
ከዘንድሮው የፀረ-ሙስና ቀን አከባበር ጎን ለጎን የተቋማት አመራር ኃላፊዎች ሃብት ምዝገባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው 20ኛው ዓለምአቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ከበዓሉ ሁነቶች ጎን ለጎን የተቋማት አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ሃብት ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
የፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የዘንድሮውን የፀረ ሙስና ቀንን በማስመልከት መግለጫ…
በቻይና የሚደገፈው የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ላቦራቶሪ በኢትዮጵያ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የሚደገፈው የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) ላቦራቶሪ በኢትዮጵያ ተከፍቷል፡፡
የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) በቻይና የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለትን ከፍተኛ ላቦራቶሪ…
የአዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ከአውሮፓ የፈጠራ ባለቤትነት ቢሮ ጋር የትብብር ሥምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን እና የአውሮፓ የፈጠራ ባለቤትነት ቢሮ ሦስተኛው ለሁለት ዓመታት የሚቆይ የሥራ ዕቅዳቸው ላይ በትብብር ለመሥራት ተፈራርመዋል፡፡
ሥምምነቱ ከፈረንጆቹ 2023 እስከ 2025 የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል።…
በአቶ አሻድሊና አቶ ጥላሁን የተመራ ልዑክ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የተመራ ልዑክ በአሶሳ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በአሶሳ ከተማና ዙሪያው በሌማት…
በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የአገልግሎት መሟላት የቀጠናውን አቅም እንደሚያሳድግ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መሟላት የቀጠናውን አቅም እንደሚያሳድግ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ጋር የመግባቢያ…
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አድማሱ ዳምጠው እንደገለጹት÷ የመግባቢያ ሠነዱ በዩኒቨርሲቲው…
የብልጽግና ፓርቲ ልዑካን ቡድን በቻይና የመስኖ ፕሮጀክትን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ በቻይና የዱጂያንግያን የመስኖ ፕሮጀክትን ጎብኝቷል፡፡
የመስኖ ፕሮጀክቱ ጎርፍን ለመከላከል፣ ለቼንዱ አካባቢ የመስኖ ውሃ ምንጭ ለመሆን እና ለቱሪስት መዳረሻነት ለማገልገል…
የኢጋድ 2ኛው የተቀናጀ የፍልሰተኞች ጉዳይ ምላሽ የሕግ ማዕቀፍን የተመለከተ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ሁለተኛው የተቀናጀ የፍልሰተኞች ጉዳይ ምላሽ የህግ ማዕቀፍን የተመለከተ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።
ኢጋድ የመጀመሪያውን የፍልሰተኞች ጉዳይ ምላሽ የህግ ማዕቀፍ ከፈረንጆቹ 2015…