Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ ቻይና ገበያ እንዲገቡ መፈቀዱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና መንግስት የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ ቻይና ገበያ እንዲገቡ መፍቀዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ በአጠቃላይ ንግድ በሚነገድባቸው 6 ሺህ 422 ምርቶች ውስጥ 1 ሺህ 644 ምርቶች ከቀረጥና ኮታ ነጻ ማስገባት…

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅታዊ የከተማዋ ጉዳዮች ዙሪያ ከነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅታዊ የከተማዋ ጉዳዮች ዙሪያ ከነዋሪዎች ጋር ተወያዩ። ከንቲባ አዳነች በወቅታዊ የመዲናዋ ጉዳይ ላይ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሔዳቸውን ገልፀዋል።…

ሑመራ በድጋሚ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኘች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባት የቆየችው የሑመራ ከተማ ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል በድጋሚ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በአገልግሎቱ የጎንደር ዲስትሪክት ዳይሬክተር ሞገስ አበራ እንደገለጹት÷ ከተማዋ…

የቤሕነን ታጣቂ ቡድን በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ታጣቂ ቡድን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት በመፈራረም የሰላም እና የልማት ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት ዛሬ ወደ ክልሉ ገብቷል። ታጣቂ ቡድኑ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል…

ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያሳድጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ዳንኤል እንድሪስ ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያሳድጉ ጥሪ አቀረቡ ፡፡   በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ…

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር በጅማ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛኦ ዚያን በጅማ ከተማ በቻይና መንግስት ድጋፍ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡   አምባሳደር ዛኦ ዚያን በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከልየሚደረጉ ትብብሮች የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት…

በትግራይ ክልል 98 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የሰብዓዊ እርዳታ መሰራጨቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ከ98 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የሰብዓዊ እርዳታ መሰራጨቱን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በትግራይ ክልልድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚከናወነውያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ…

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

  አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡   አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ባደረበት ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከቤተሰቦቹ አረጋግጧል፡፡…

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ የሚሠራ የልኅቀት ማዕከል ሊያቋቁም ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦች እንዲሳኩ በጥናትና ምርምር የሚደግፍ የልኅቀት ማዕከል ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን ገለጸ። ማዕከሉ በዘላቂ ልማት ግቦች አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገው ፕሮጀክት አካል እንደሆነም አመልክቷል።…

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የኢፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሥራ ኃላፊዎች ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና የኢፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሥራ ኃላፊዎች ተወያይተዋል። ሁለቱ ተቋማት የዓለም አቀፍና የሀገር አቀፍ የቀይ መስቀል መርኅዎችን መሠረት በማድረግ አብሮ ለመሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ዉይይት…