Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቤልጂየም ብራሰልስ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በ115ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት ጉባዔ ላይ…

በሐረሪ ክልል የሙስና ወንጀልን ለመከላከል የሚያስችል ኮሚቴ ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የሙስና ወንጀልን ለመከላከል እና የወንጀሉን ተዋንያን ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ክልላዊ ኮሚቴ ተቋቁሟል። ኮሚቴው በተለያዩ መዋቅሮች በተደራጀ መልኩ የሚፈፀም የመሬት ነክ ሙስና፣ ከግብር፣ ከግዥ፣ ለፕሮጀክቶች፣ ከግንባታ ፍቃድ፣…

ህዝቡን ከፀጥታ ስጋት ለማላቀቅና አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን በትኩረት እየተሰራ ነው-ዶክተር አለሙ ስሜ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝቡን ከፀጥታ ስጋት ለማላቀቅና አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን መንግስት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር አለሙ ስሜ ገለፁ ። ዶክተር አለሙ በምስራቅ ሸዋ…

አቶ ደመቀ ኢስዋቲኒ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላሳየችው ሚዛናዊ አቋም ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከኢስዋቲኒ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቱሊሲል ድላድላ ጋር ተወያይተዋል፡፡   በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ኢስዋቲኒ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡…

የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በየደረጃው ያለው አመራር ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቲቢ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እንዲሁም አስፈላጊውን የሀገር ውስጥ ፋይናንስ ለማሳደግ በየደረጃው ያለው አመራር ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጤና ሚኒስቴር አስገነዘበ፡፡ በአፍሪካ የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ፖለቲካዊ…

ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል -ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ፡፡   በክልሉ17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ቀን…

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አራት ወራት 22 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በአራት ወራት ውስጥ በመደበኛ እና የማዘጋጀ ቤት የገቢ ማሰባሰብ ስራ 22 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡ የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ÷በክልሉ ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ…

የአማራ ክልል ማዕድን ልማት ቢሮ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ለሚገነቡ 11 ባለሃብቶች የምርመራ ፈቃድ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ለሚገነቡ 11 ባለሃብቶች የምርመራ ፈቃድ መስጠቱን የአማራ ክልል ማዕድን ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በሲሚንቶ እጥረት ምክንያት ግንባታዎች ከመጓተት እስከ መቆም መድረሳቸው ተገልጿል፡፡…

በአፋር ክልል በቅርቡ ተፈናቅለው ከነበሩት 69 ሺህ ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ወደ ቀያቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በቅርቡ ከተፈናቀሉ 69 ሺህ ሰዎች መካከል 34 ሺህዎቹ ወደ መኖሪያ ቀያቸው መመለሳቸውን የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራርና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ። በኮሚሽኑ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክተር ማሒ ዓሊ፥ በሰው ሠራሽ ችግር…

የኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ሰላም አስከባሪ ኃይሎች የጥምር ውጊያ ልምምድ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአትሚስ ሴክተር አራት 7ኛ ዙር ሰላም አስከባሪ ሃይል ከጂቡቲ ሰላም አስከባሪ ኃይል ጋር ግዳጅን መሰረት ያደረገ የጥምር ውጊያ ልምምድ አድርገዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች የጋራ ጥምር ውጊያ ልምምድ ማድረጋቸው ቀጣይ…