Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ አጭሯ ሴት ልጅ በሠላም ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ61 ሴንቲ ሜትር ርዝመት በአፍሪካ ድንቃ ድንቅ መዝገብ በኢትዮጵያ አጭሯ ሴት ተብላ የተመዘገበችው ኤሻሌ ወርቁ ሴት ልጅ በሠላም ተገላግላለች። ኤሻሌ ወርቁ በወላይታ ሶዶ ዞን በሚገኘው ክርስቲያን ሆስፒታል ጠዋት 3 ሠዓት ላይ መውለዷን የአፍሪካ…

በትምህርትና ምዘና ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ ተቀባይነት የለውም -የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርትና ምዘና ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ ተቀባይነት የለውም ሲል የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ገለጸ፡፡ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩን አስመልክቶ በስተላለፈው መልዕክት÷ በትምህርትና ምዘና ላይ የሚደረግ አሉታዊ ዘመቻ በእውቀት ላይ…

የብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩ 100ኛ ዓመት የልደት በዓል ሊከበር ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብርጋዴር ጀነራል ታደሰ ብሩ ፋውንዴሽን የጀነራሉን 100ኛ ዓመት የልደት በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሊያከብር መሆኑን ገለጸ። ፋውንዴሽኑ የበዓል አከባበሩን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫውም ፥ የበዓሉ መከበር ዋነኛ…

የቡና ገለባ ከተበላሸ ለውዝ ጋር ቀላቅሎ የምግብ ዘይት ሲያመርት በተገኘ ተቋም ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቀጨኔ አካባቢ የቡና ገለባ ከሻገተ ለውዝ ጋር በመቀላቀል የምግብ ዘይት ሲያመርት በተገኘ ተቋም ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡…

ቦርዱ በስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ የጊዜ ሠሌዳ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ የትግበራ አፈጻጸም ዝርዝር ዕቅድ ማሳያ የጊዜ ሠሌዳ ይፋ አደረገ፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ…

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከደቡበ ኮሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የደቡበ ኮሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ኪም ጂን-ፒዮን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል…

አቶ አህመድ ሺዴ ከዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ከዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ…

አቶ ዑመር ሁሴን ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት የአፍሪካ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት የአፍሪካ ተወካይ አቶ አበበ ሃይለገብርኤል ጋር ተወያዩ ፡፡ በውይይታቸውም የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው…

አዳዲስ የሥራ ፈጠራ የቢዝነስ ሀሳብ የያዙ አስር የኢትዮጵያ ድርጅቶች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ 2022 እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዳዲስ የሥራ ፈጠራ የቢዝነስ ሀሳብ የያዙ አስር የኢትዮጵያ ድርጅቶች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፉ ነው። የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ የተመራ የመንግሥት እና አዳዲስ የሥራ ፈጠራ…

ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን አንገብጋቢ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል መሆን አለበት- ከፍተኛ አመራሮች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስር የሰደዱ አንገብጋቢ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል መሆን እንዳለበት ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ገለጹ፡፡ የክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች እና ከፍተኛ አመራሮች ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ባቀረበው…