Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የመጠጥ ውሃ ተቋማትና መጸዳጃ ቤቶች ይገነባሉ – የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በ2015 ዓ.ም በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የመጠጥ ውሃ ተቋማት፣ የማህበረሰብና የጋራ መጸዳጃ ቤቶች ለመገንባት እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡ ፕሮጀክቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ…

ከሰሞኑ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት” በሚል የወጣው ሪፖርት ፖለቲካዊ ሸፍጥ አለበት – የሕግ ምሁራን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰሞኑ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት” በሚል የወጣው ሪፖርት ከሣይንሳዊ መንገድ ይልቅ ፖለቲካዊ ሸፍጥን የተከተለ ነው ሲሉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተሠራው ምርምር የተሳተፉ የሕግ ምሁራን ተናገሩ፡፡ ምሁራኑ ለፋና ብሮድካስንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷…

መንግስት የዓለም አቀፉ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጡትን ሪፖርት ውድቅ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጡት ሪፖርት የፖለቲካ አጀንዳ ለመፍጠር ታልሞ የተሰራ ነው ሲል ውድቅ አድርጎታል። ቡድኑ ላለፉት 10 ወራት በኢትዮጵያ ተፈፅመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን…

በ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ በ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ከ60 በላይ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች እንደሚገነቡ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የውሃ አና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በአሸባሪው…

የቻይና ዓለም አቀፍ የልማት ኢኒሼቲቭ የልማት ግቦችን ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ ነው – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለመተግበር ትብብር እና አጋርነት ቁልፍ ጉዳዮች መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ አቶ ደመቀ በኒውዮርክ ከተማ እየተካሄደ ካለው…

በጋምቤላ ክልል በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በጋምቤላ ክልል በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው መድኃኒት፣ አልባሳትና ተጨማሪ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ተስፋሁን ጎበዛይ ድጋፉን ዛሬ ለክልሉ…

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ችግር ለመቅረፍ ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተስተዋለ ያለውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ ያለመ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ…

የሙያተኝነት መስፈርትን ሳያሟላ የተዘጋጀውን የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባላት እንዲቃወሙ ኢትዮጵያ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ያቀረበውን ከደረጃ በታች የወረደ ሪፖርት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባላት እንዲቃወሙ ኢትዮጵያ ጥሪ አቀረበች። በጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ…

በንግድ ሽፋን የጦር መሳሪያ ሲነግድ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በመጠጥ ንግድ ሽፋን የጦር መሳሪያ ሲነግድ የነበረ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና ተተኳሽ ጥይቶችን ጨምሮ 80…

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጡት መግለጫ ፖለቲካዊ ፍላጎትን ያዘለ ነው – በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጡት መግለጫ ፖለቲካዊ ፍላጎትን ያዘለ መሆኑን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች ባለፈው ነሐሴ ወር የፀጥታው…