Browsing Category
የሀገር ውስጥ ዜና
ከነበሩብን ጫናዎች አንጻር የ2014ዓ.ም አፈጻጸም ስኬታማ ነበር- አቶ ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገራችን ላይ ከነበሩ ዘርፈ ብዙ ጫናዎች አንጻር የ2014ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ስኬታማ ነበር ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የ2014ዓ.ም የዕቅድ…
የቲቢ ቤተ ሙከራ ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ስብሰባውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡብ አፍሪካ የጤና ማህበረሰብ ግሎባል ፈንድ ክልላዊ የቲቢ ቤተ ሙከራ ማጠናከሪያ ፕሮጀክት 8ኛው የአስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት…
ዶክተር በለጠ ሞላ ከቶኒ ብሌር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ከቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት መስራች፣ ሊቀመንበር እና የቀድሞው የታላቋ ብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ዶክተር በለጠ ኢንስቲትዩቱ…
የካፋ እና የከምባታ ጠምባሮ ዞኖች ለሰራዊቱ ሃብት እያሰባሰቡ ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፋ እና የከምባታ ጠምባሮ ዞኖች አሸባሪው ህወሓት ለ3ኛ ጊዜ የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስና በድል ለማጠናቀቅ ለመከላከያ ሠራዊት ሃብት እያሰባሰቡ ነው፡፡
ዛሬ በካፋ ዞን “እኔም ለሀገሬ ወታደር ነኝ" በሚል መሪቃል ለመከላከያ ሠራዊት በተደረገ…
ከተማ አስተዳደሩ በጥበበኛ እጆች የሚሰሩ የዕደ-ጥበብ ስራዎችን ያበረታታል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጥበበኛ እጆች የሚሰሩ መሰል የዕደ-ጥበብ ስራዎችን ያበረታታል፣ ድጋፍ ያደርጋልም ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች…
ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአስር ዓመታት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ኢትዮጵያ በጣሊያን ጦር በግፍ በተወረረችበት ወቅት ለአራት ዓመታት ያህል…
አቶ ሙስጠፌ ከዴንማርክ የስደተኞች ም/ቤት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከዴንማርክ የስደተኞች ምክር ቤት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጀምስ ክርቲስን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በክልሉ በተከሰተው በድርቅ ሳቢያ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው…
ከተማ አስተዳደሩ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የተለያዩ የምግብ ነክና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ 191 ሰንጋዎች፣ 524 በግ፣ 287 ኩንታል በሶ፣ 151 ኩንታል ዳቦ ቆሎና 9 ሺህ 949 ጫማዎችን…
ከተማ አስተዳደሩ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአምራች ቀንን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡
በውይይቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት…
አሊባባ ግሩፕ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የትብብር ስምምነት አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014፣ (ኤፍ ቢ ሲ) አሊባባ ግሩፕ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለስራ ፈጣሪዎች ስልጠና ለመስጠት የሚያስችላችውን ስምምነት አድርገዋል።
ስምምነቱ አሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የቴክኖሎጂ ስራ ፈጣሪዎች ስልጠና ለመስጠት እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማህበር…