Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የንግድ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ከ30 አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ የንግድ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ከ30 አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን የከተማዋ ንግድ ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ ሀቢባ ሲራጅ የንግድ ተቋማት የሥራ ሰዓት መራዘምን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ÷ በከተማዋ ያለውን ምቹ ሁኔታ…

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ት/ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። በቢሮው የእቅድ ዝግጅትና ክትትል…

በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ማቋቋም አተገባበር ላይ የማህበረሰብ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ማቋቋምና ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል አተገባበር ሂደት የሕብረተሰቡ ሚና ምን መሆን እንዳለበት የሚመክር መድረክ በመቐለ ከተማ ተካሄደ። በምክክሩ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የትግራይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ…

በጎንደር ከተማ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር ከተማ በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትንና የሰላምን መረጋገጥ የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። ሰልፉ መንግስት ሰላምን ለማስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በመደገፍና የልማት ተግባራትን ለማገዝ ታሳቢ ያደረገ ነው።…

በባሕር ዳር ከተማ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በባሕር ዳር ከተማ "ሰላም ለሁሉም ፤ ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሃሳብ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። በሕዝባዊ ሰልፉ ለክልሉ የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሰላምና ልማት መሆኑን የሚያንጸባርቁ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡ ከተላለፉ…

በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ሕዝባዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በአማራ ክልል እየተከናወነ ያለው ሕግ የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚጠይቁ ሕዝባዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው። ሰልፈኞቹ በክልሉ መንግሥት እያካሄደ ያለውን ሕግ የማስከበር ዘመቻ የሚደግፉ መልዕክቶችን…

በኢትዮጵያና ሶማሊያ ድንበር የሚገኘው ጦር በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያና ሶማሊያ ድንበር የሚገኘው ጥምር ጦር በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ የጥምር ጦሩ አመራሮች በወቅታዊ የሠላም ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂደዋል። በዚሁ ወቅት በመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ የሀይል ስምሪት…

አየር መንገዱ “ኤር ኮንጎ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አየር መንገድ አቋቁሞ ስራ አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በመሆን “ኤር ኮንጎ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አየር መንገድ አቋቁሞ በይፋ ስራ አስጀመረ። ኤር ኮንጎ በሁለት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ሰባት ኤርፖርቶች…

በአማራ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 154 የታጠቁ ኃይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 154 የታጠቁ ኃይሎች መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለዋል። በከለላ ወረዳ ሊጮ አካባቢ ተመሥርተው በአባ ጋስጫ፣ በሪማ፣ በጎረንጂ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ታጣቂዎች "የገባንበት…