Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ስፓርት

6ኛው የብዙሃን ስፖርት በመስቀል አደባባይ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስድስተኛው ዙር የብዙሃን ስፖርት መርሃ-ግብር ዛሬ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል። አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግን ባህል ያደረገ ከተማ እና ህብረተሰብ መፍጠርን ዓላማ ባደረገው በዚህ ሁነት በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና፣ ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ተደርገዋል። አዲስ አበባ ላይ ሃዲያ ሆሳዕናን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል። ቡናማዎቹ ጨዋታውን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት…

ጋና በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞችን አሰናበተች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋና እግር ኳስ ማህበር በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብሄራዊ ቡድን የአሰልጣኝ አባላት ማሰናበቱን አስታወቀ። ማህበሩ የወንዶችና የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ እና ረዳቶቻቸውን ከስራ ማሰናበቱን አስታውቋል። ስንበቱ በሁለቱም ጾታዎች የታዳጊ፣…

በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደቀጠለ ነው፡፡ በርካታ ታዳጊ አትሌቶች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከታህሳስ 20 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም በመካሄድ…

የአዲስ አበባ የብሄራዊ ስታዲየም ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስራው ከ4 ዓመት በፊት የተጀመረው በኢትዮጵያ ግዙፍ የተባለውና በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው ብሄራዊ ስታዲየም የመጀመሪያው ምእራፍ የግንባታ ተጠናቆ፤ ሁለተኛ ምእራፍ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀምር ተገለፀ።   በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት አንድ ጨዋታ መቐለ ላይ ተካሂዷል። በትግራይ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል። ለመቐለ 70 እንደርታ አማኑኤል ገብረሚካኤል የማሸነፊያ…

ሀገራዊ የስፖርት ማሻሻያ የንቅናቄና ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በክልል ደረጃ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀገራዊ የስፖርት ማሻሻያ የንቅናቄና ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በክልል ደረጃ እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩ እስከ ጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፥ በየደረጃዉ የሚገኙ የስፖርት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል።…

የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 46 ታዳጊዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሞተር ስፖርት ውድድር ያሰለጠናቸውን 46 ታዳጊዎች አስመረቀ።   ማህበሩ በሁለት ዙር 60 ታዳጊ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለሁለት ተከታታይ ወራት ሲያሰለጥን የቆየ ሲሆን ከነዚህ…

በፕሪምየር ሊጉ ወልቂጤ ፣ ጅማ አባ ጅፋርና ሲዳማ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት በዛሬው ዕለት ስድስት ጨዋታዎችን በክልል ከተማዎች አስተናግዷል፡፡ በዚህም ወደ ጅማ ያቀናው ቅዱስ ጊዮርጊስ በጅማ አባ ጅፋር 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡ የጅማ አባ ጅፋርን የማሸነፊያ ግቦች ብዙዓየሁ…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 6 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሰ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ቀጥለው ይካሄዳሉ። በዛሬው እለት ስድስት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፥ ሁሉም ጨዋታዎች በክልል ከተሞች የሚደረጉ ይሆናል። በዚህም ወላይታ ዲቻ ከወልቂጤ ከተማ፣ ስሹል ሽረ…