Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
የኒውክሌር ባለቤት በሆኑ ሀገራት መካከል የሚፈጠር ግጭት ወደ ዓለምአቀፋዊ ጥፋት ያመራል – ሰርጌ ላቭሮቭ
አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኒውክሌር ባለቤት በሆኑ ሀገራት መካከል የሚፈጠር ማንኛውም ግጭት ወደ ዓለም አቀፋዊ የኒውክሌር ጦርነት ሊያመራ ይችላል ሲሉ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ አስጠነቀቁ፡፡
ላቭሮቭ የኒውክሌር ባለቤት በሆኑ ሀገራት መካከል የሚኖር…
የ“አይ ኤስ” መሪ አቡ አል-ሐሰን አል-ሐሺም አል-ቁራሺ ተገደለ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑ “ካሊፍ” ብሎ የሚጠራው የ “አይ ኤስ አይ ኤስ” መሪ አቡ አል-ሐሰን አል-ሐሺም አል-ቁራሺ መገደሉ ተነግሯል፡፡
አቡ አል-ሐሰን አል-ሐሺም አል-ቁራሺ በውጊያ ላይ መገደሉን የአይ ኤስ ሽብር ቡድን ምክትል መሪ ማስታወቁን አርቲ እና…
ለሃንጋሪ የተፈቀደው 13 ቢሊየን ዩሮ እንዳይለቀቅ የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ምክረ-ሃሳብ አቀረበ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት ለሃንጋሪ የፈቀደው የ13 ቢሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ እንዳይለቀቅ የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ምክረ-ሃሳብ አቀረበ፡፡
የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ÷ የገንዘብ ድጋፉ እንዲያዝ ሲል በምክንያትነት ያቀረበው ሃንጋሪ የአውሮፓን የኅግ…
ቱርክ ከሶሪያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር ላይ እየከረረ በመጣው ወታደራዊ ፍጥጫ ዙሪያ ከኢራን ጋር መከረች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂያን እና የቱርክ አቻቸው ሜቭሉት ካቩሶግሉ በቱርክ እና በሶሪያ ድንበር እየተባባሰ ባለው ወታደራዊ ውጥረት ላይ መምከራቸው ተሰማ፡፡
ሚኒስትሮቹ በስልክ በነበራቸው ውይይት በሀገራቱ መካከል ቀጣይነት…
የቀድሞው የቻይና ፕሬዚዳንት ጂያንግ ዜሚን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የቻይና ፕሬዚዳንት ጂያንግ ዜሚን በ96 ዓመታቸው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ጂያንግ ዜሚን ከደም ካንሰር ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻቸው ላይ በደረሰባቸው ፅኑ ሕመም ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የቻይና…
አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል ከማስወንጨፏ በፊት ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ሥርዓት ልትዘረጋ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎች ከመወንጨፋቸው በፊት ቅድመ-ማስጠንቀቂያ መሥጠት የሚችል ሥርዓት ልትዘረጋ መሆኑን አሜሪካ አስታወቀች፡፡
በትናንትናው ዕለት መቀመጫውን በዋሺንግተን ያደረገው ሚቼል የተሠኘው የአሜሪካ የዓየር እና የጠፈር ምርምር ተቋም በዘርፉ…
ቻይና ከሩሲያ ጋር በኃይል ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከሩሲያ ጋር በኃይል ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንት ሺ 4ኛው የቻይና-ሩሲያ የኃይል ፎረምን አስመልከተው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የኃይል ዘርፍ ትብብር ለሀገራቱ የሁለትዮሽ…
በካሊፎርኒያ የተከሰተው ድርቅ የአሜሪካን የምግብ ዋስትና አደጋ ላይ ይጥላል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያስተናገደችው ከባድ የድርቅ አደጋ ከሠብል ምርት ታገኝ የነበረውን ቢያንስ 3 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ገቢ እንዳሳጣት ጥናት አመላከተ፡፡
ካሊፎርኒያ ከአሜሪካ ግዛቶች በግብርና ምርቷ በግንባር…
በደቡብ ኮሪያ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኮሪያ ያንግያንግ እና ጋንግዎን ግዛት በደን ላይ የተከሰተን እሳት ለማጥፋት በሥራ ላይ የነበረ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
ሄሊኮፕተሩ የተከሰከሰው በደቡብ ኮሪያ ያንግያንግ እና ጋንግዎን ግዛት…
ቻይና ለዓለም ሰላም እና መረጋጋት ከሰሜን ኮሪያ ጋር በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ ናት- ሺ ጂንፒንግ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለዓለም ዘላቂ ሰላም እና ልማት ከሰሜን ኮሪያ ጋር በቅንጅት ለመስራትቁርጠኛ ናት ሲሉ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ገለጹ፡፡
የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ሰሜን ኮሪያ ታይቶ ባማይታወቅ ሁኔታ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሚሳኤሎች ማስወንጨፏን ተከትሎ…