Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን ለቆ መውጣት ሃገሪቱን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እንዳይከታት ተሰግቷል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን ለቆ መውጣት በሃገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል ሲሉ ከፍተኛ የአሜሪካ ወታደራዊ አዛዥ አስጠነቀቁ፡፡
በአፍጋኒስታን የአሜሪካ መራሹ ጦር አዛዥ ጀኔራል ስኮት ሚለር፥ የአሜሪካ ጦር ከሃገሪቱ…
ሆንግ ኮንግ ከእንግሊዝ የሚደረጉ በረራዎችን በሙሉ አገደች
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሆንግ ኮንግ ከእንግሊዝ የሚደረጉ በረራዎችን በሙሉ ማገዷ ተሰማ፡፡
ሃገሪቱ እገዳውን ያደረገቹ አዲስ (ዴልታ ) ዝርያ ያለው የኮቪድ 19 ቫይረስ በእንግሊዝ ከመከሰቱ ጋር ተያይዞ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሃገሪቱ ከእንግሊዝ ወደ ሆንግ ኮንግ የሚደረግ…
በፍሎሪዳ በደረሰ የህንጻ መደርመስ እስካሁን 150 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት በደረሰ የህንጻ መደርመስ አደጋ እስካሁን 150 የሚሆኑ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም፡፡
ባሳለፍነው ሃሙስ በተከሰተው በዚህ አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች ቁጥር ዘጠኝ ሲደርስ÷ 150 የሚሆኑት ደግሞ ደብዛቸው ጠፍቷል ነው…
አሜሪካ በኢራን በሚደገፉ የኢራቅ እና ሶሪያ ታጣቂ ቡድኖች ላይ የአየር ላይ ጥቃት ፈጸመች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢራን በሚደገፉ የኢራቅ እና የሶሪያ ታጣቂ ቡድኖች ላይ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተሰምቷል፡፡
የአየር ላይ ጥቃቱ ታጣቂ ቡድኖች ኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ለፈጸሙት የድሮን ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ መሆኑን የአሜሪካ መከላከያ…
ሱዳን በዳርፉር የጦር ወንጀል የፈጸሙ የቀድሞ ባለስልጣናትን አሳልፋ ለመስጠት ተስማማች
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን በዳርፉር የጦር ወንጀል በመፈጸም የሚፈለጉ የቀድሞ ባለስልጣናትን ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፋ ለመስጠት ተስማምታለች፡፡
ውሳኔው በቅርቡ በሱዳን ጉብኝት ያደረጉት የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተሰናባች ዓቃቤ…
የጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ 22 ዓመት ከ6 ወር የእስር ቅጣት ተወሰነበት
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ-አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ ዴሬክ ሾቪን 22 አመት ከ6 ወራት የእስር ቅጣት ተወሰነበት፡፡
የቀድሞው ፖሊስ ባልደረባ የሆነው ሾቪን ጆርጅ ፍሎይድን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉ ይታወሳል፡፡
ባለፈው የፈረንጆቹ አመት የተፈጸመው ግድያ…
የዓለም ባንክ ለደቡብ ሱዳን የ113 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ለደቡብ ሱዳን የ113 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ በደቡብ ሱዳን ያለውን የምግብ እጥረት ለማቃለል ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የአካባቢውን አርሶ አደሮች ለመደገፍ የሚውል መሆኑም ነው የተገለጸው።…
በካናዳ በትምህርት ቤት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የማይታወቁ መቃብሮች ተገኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ የሚገኝ አንድ ቡድን በ ሳስኬችዋን አውራጃ ውስጥ የቀድሞ የመኖሪያ ቤት ትምህርት ቤት በሚገኝበት ቦታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምልክት የሌላቸውን መቃብሮች ማግኘቱን ገለጸ፡፡
ባሳለፍነው ወር ካውስስ በሳስኬችዋን ግዛት በሚገኘው የማሪቫል የህንድ…
አሜሪካ ሀሰተኛ መረጃዎችን ያሰራጫሉ ያለቻቸውን የኢራን ድረ ገጾች አገደች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣2013 (ኤፍ ቢሲ) አሜሪካ ሀሰተኛ እና የተዛቡ መረጃዎችን ያሰራጫሉ ያለቻቸውን የኢራን ድረ ገጾች ከኢንተርኔት ማገዷ ተሰምቷል፡፡
የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ ባለቤትነታቸው የኢራን መንግስት የሆኑ 33 ድረ ገጾች እና የሃውቲ አማጺያን…
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያኢር ላፒድ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት ሊያደርጉ ነው፡፡
ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው እንደ አዲስ ከጀመሩ ወዲህ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ…