Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

ዮሲሂዴ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በይፋ ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዮሲሂዴ ሱገ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በይፋ ተመረጡ፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሲሂዴ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤን በመተካት ነው የተመረጡት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰሞኑ የፓርቲያቸው ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው…

በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘው ሰው ቁጥር ከ 5 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘባት ሰው ቁጥር ከ5 ሚሊየን ማለፉን አስታወቀች፡፡ በህንድ የተመዘገበው ይህ ቁጥር ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁ አገራት መካከል ሁለተኛዋ ያደርጋታል፡፡ በሀገሪቱ ከቅርብ ቀናት ወዲህ በየዕለቱ 90 ሺህ ሰዎች…

የኬንያ አየር መንገድ ዳግም ወደ ሶስት የአፍሪካ ሃገራት በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኬንያ አየር መንገድ ዳግም በሶስት የአፍሪካ ሃገራት የንግድ በረራ ሊጀምር መሆኑ ተገለፀ፡፡ አየር መንገዱ በረራ የሚጀምርባቸው ሃገራትም ጋና ፣ ሴራሊዮን እና ላይቤሪያ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዚህም በሳምንት አራት ጊዜ ወደ አክራ ፣…

በአፍሪካ እስካሁን ከ12 ሚሊየን በላይ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተካሂደዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ኮቪድ-19 ምርመራ አጠናክሮ ለመቀጠል ጥሪ መደረጉን ተከትሎ እስካሁን ከ12 ሚሊየን በላይ የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል፡፡ በዚህም እስካሁን ከተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 10 በመቶ ያክሉ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ እንደ…

የምስራቅ ሊቢያ መንግስት ስልጣን ለቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካሊፋ ሃፍጣር ስር የሚገኘው የምስራቅ ሊቢያ መንግስት ከቤንጋዚ ተቃውሞ በኋላ ስልጣን መልቀቁ ተሰምቷል። በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ አልታኒ የሚመራው በምስራቅ ሊቢያ መንግስት በኑሮ ውድነት እና ሙስና ምክንያት በርካታ ተቃውሞዎች ከተነሱ በኋላ…

ቻይና የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለመላ ዜጎቼ አያስፈልግም አለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና በዚህ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እንጂ ለመላ ዜጎች ክትባቱ እንደማይስፈልግ የሀገሪቱ ከፍተኛ የጤና ባለስልጣን ገለፁ።   የቫይረሱ ክትባት ጥቅም ላይ በሚውልበት ወቅት በሽታውን…

ተቃውሞ የበረታባቸው የቤላሩሱ ፕሬዚዳንት ሉካሼንኮ ከ ፑቲን ጋር ለመምከር ወደ ሩሲያ አቅንተዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተቃውሞ የበረታባቸው የቤላሩሱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ከሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመምከር ወደ ሶቺ አቅንተዋል። ሉካሼንኮ አገራቸው ከአንድ ወር በፊት ያደረገችውን ምርጫ ተከትሎ ተቃውሞ በርትቶባቸዋል። በምርጫው ሉካሼንኮ…

ዮሲሂዴ ተሰናባቹን የጃፓን ገዢ ፓርቲ መሪ ሺንዞ አቤን በመተካት የፓርቲው መሪ በመሆን ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዮሲሂዴ ሱገ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትርና የገዢው ፓርቲ መሪ ሺንዞ አቤን በመተካት የጃፓን ሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ በመሆን ተመረጡ፡፡ ዮሲሂዴ ሱገ የፓርቲው መሪ ሆነው በመመረጣቸው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚያደርጉትን ጎዞ ያቀልላቸዋል…

በዓለም የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 29 ሚሊየንን ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ29 ሚሊየን ማለፉን የወርልድ ኦ ሜትር መረጃ ያሳያል። እንደ መረጃው በዓለም አቀፍ ደረጃ እስካሁን 29 ሚሊየን 185 ሺህ 779 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መያዛቸው ተረጋግጧል።…

የማሊ ወታደራዊ አመራሮች ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የአስራስምንት ወራት የሽግግር ጊዜ መንግስት ለማቋቋም ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማሊ ወታደራዊ አመራሮች ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የአስራስምንት ወራት የሽግግር ጊዜ መንግስት ለማቋቋም ተስማሙ፡፡ የሚቋቋመው ጊዜያዊው የሽግግር መንግስት በወታደሮች ወይንም በሲቪሎች ሊመራ ይችላል ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡ እዚህ ውሳኔ…