Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
እስራኤል በሊባኖስ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በሊባኖስ የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ይዞታዎች ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ መወሰኗ ተሰምቷል፡፡
ውሳኔው ሂዝቦላህ የእስራኤል ወታደራዊ ማዕከላትን የሚያሳይ በድሮን የተቀረጸ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የተላለፈ እንደሆነ ተነግሯል።…
ቻይና በዓለም ትልቁን የትራንስፖርት ማሳለጫ ገነባች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በዓለም ትልቁን የትራንስፖርት ማሳለጫ በከፍተኛ ወጪ መገንባቷ ተመላክቷል፡፡
የቻይና የማሳለጫ መንገዶች ርዝማኔ በፈረንጆቹ 2023 ከ6 ሚሊየን ኪሎ ሜትሮች በላይ ማደጉ ተገልጿል፡፡
ይህም በዓለም ትልቁ የፍጥነት ባቡር፣ የፈጣን መንገድ…
ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለምታደረግው ጦርነት ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ የገቡት የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን በወታደራዊ ትርዒት የታጀበ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ፑቲን ባለፈው መስከረም ወር ኪም ጆንግ ኡን ባቀረቡላቸው…
በካሊፎርኒያ 50 ኪሎ ሜትር ካሬ የሸፈነ ሰደድ እሳት ተቀስቅሶ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ከሎስ አንጀለስ ሰሜን ምዕራብ የተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት 50 ካሬ ኪሎ ሜትር ካሬ ቦታ እንደሸፈነና ነዋሪዎች እንዲለቁ ማስገደዱ ተገለጸ።
ሰደድ እሳቱ ከአንድ ሺህ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ ማስገደዱን…
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የጦር ካቢኔያቸውን በተኑ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሀገሪቱን ጦር ካቢኔ መበተናቸው ተሰምቷል፡፡
ውሳኔው የእስራኤል የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንትዝ ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የጦር ካቢኔው መበተን ውሳኔ የእስራኤል…
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ ዕርዳታ እንዲገባ በሚል ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን ገታች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ዋና መንገድ ተጨማሪ ዕርዳታ እንዲገባ ወደፊት ገደቡ መነሳቱ እስከሚገለጽ ድረስ በየቀኑ ለተወሰኑ ሠዓታት ወታደራዊ እንቅስቃሴውን መግታቱን አስታወቀ፡፡
እንደ ጦሩ ገለጻ÷ ከኬረም- ሻሎም ማቋረጫ ወደ…
ህንድ በእሳት አደጋ ህይወታቸውን ያጡ 45 ዜጎቿን አስከሬን ከኩዌት ወሰደች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህንድ አየር ኃይል በኩዌት ህንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ህይወታቸው ያለፈ የ45 ዜጎች አስከሬን ወደ ሀገራቸው አምጥቷል።
የእሳት አደጋው የተከሰተው ከትናንት በስቲያ በኩዌት በማንጋፍ ከተማ 176 ህንዳውያን ሰራተኞች በሚኖሩበት ሕንፃ ላይ ነው።…
የቡድን 7 ሀገራት የሩሲያ ንብረቶችን በዋስትና በመያዝ 50 ቢሊየን ዶላር ብድር ለዩክሬን ፈቀዱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን 7 ሀገራት የተያዙ የሩሲያ ንብረቶችን በዋስትና በመጠቀም 50 ቢሊየን ዶላር ብድር ለዩክሬን እንዲሰጥ ተስማምተዋል፡፡
የቡድን 7 አባል ሀገራት መሪዎች በሐማስ እና እስራኤል እንዲሁም በዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት ላይ በጣልያን እየመከሩ ነው፡፡…
በኮንጎ በደረሰ የጀልባ አደጋ ከ80 በላይ መንገደኞች ህይወት ማለፉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ አቅራቢያ በሚገኝ ወንዝ ላይ 270 በላይ ተሳፋሪዎችን ጭና የነበረች ጀልባ ተገልብጣ ከ80 በላይ መንገደኞች ህይወት ማለፉን ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ትሺሴኬዲ አስታውቀዋል።
በሀገሪቱ በፈረንጆቹ የካቲት ወር ላይ…
በኩዌት የቤት ሰራተኞች በሚኖሩበት ሕንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ41 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩዌት ማንጋፍ ግዛት በመኖሪያ ሕንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ የ41 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡
አደጋው የቤት ውስጥ ሰራተኛ የሆኑ የውጭ ሀገራት ዜጎች በብዛት በሚኖሩበት ሕንጻ ላይ መከሰቱ ነው የተገለጸው፡፡
በእሳት አደጋው ቢያንስ…