Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
አሜሪካ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎችን መስጠቷ ተነገረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መስጠቷ ተሰምቷል፡፡
ዩክሬን የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በሩሲያ ላይ ቢያንስ አንድ ጊዜ መጠቀም መጀመሯን የአሜሪካ ባለስልጣናት ማረጋገጣቸውም ነው የተገለጸው፡፡…
ሩሲያና ዩክሬን ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው ድርድር አካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ዩክሬን ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው ድርድር ማካሄዳቸው ተሰማ፡፡
ጦርነት ውስጥ የገቡት ሀገራቱ ፊት ለፊት በመገናኘት ድርድር ያደረጉት በኳታር አሸማጋይነት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በፊት ለፊት ድርድሩም በጦርነቱ ምክንያት…
ግሪክ ከሰሃራ በርሃ በተነሳ አውሎ ንፋስ በአሸዋ መሸፈኗ ተነገረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ግሪክ ከሰሃራ በርሃ አሸዋ አዝሎ በተነሳ አውሎ ንፋስ በአሸዋ ብናኝ መሸፈኗ ተገለጸ፡፡
ከአፍሪካ በተነሳ ከፍተኛ አቧራ አዘል የአሸዋ አውሎ ንፋስ አቴንስ እና ሌሎች የግሪክ ከተሞች የተሸፈኑ ሲሆን፤ የሀገሪቱ ሰማይ ብርቱካናማ ቀለም ባለው ብናኝ…
ታይዋን በድጋሚ በተከታታይ ከባድ ርዕደ መሬት ተመታች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታይዋን 17 ሰዎችን ለህልፈት ከዳረገው ርዕደ መሬት አደጋ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ከትናንት ምሽት እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ በድጋሚ ለሰዓታት ከባድ በሆነ ተከታታይ ርዕደ መሬት መመታቷ ተገልጿል፡፡
በመጀመሪያ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 5 ሆኖ…
በማሌዥያ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ተጋጭተው የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማሌዥያ በበረራ ላይ የነበሩ ሁለት የሮያል ባሕር ኃይል ንብረት የሆኑ የጦር ሄሊኮፕተሮች ተጋጭተው የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ፡፡
በአደጋውም ሦስት ሴት የባሕር ኃይል መኮንኖችን ጨምሮ የ10 የሰዎች ሕይወት ማለፉን የሀገሪቱ ብዙኃን…
ፖፕ ፍራንሲስ በዩክሬን¬-ሩሲያና በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ያለው ጦርነት እንዲቆም በድጋሚ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ በዩክሬ-ሩሲያ እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በማውገዝ የእርቀ ሰላም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጳጳሱ በቫቲካን ከተማ በሚገኘው በሴንት ፒተር አደባባይ ለተሰበሰቡ ታዳሚዎች አሁንም ቢሆን በሀገራቱ…
ሰሜን ኮሪያ ወደ ምስራቅ ባህር ባላስቲክ ሚሳዔል ማስወንጨፏ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ወደ ምስራቅ ባህር ባላስቲክ ሚሳዔል አስወንጭፋለች ሲሉ የደቡብ ኮሪያ የጥምር ኃይል አዛዥ አስታወቁ፡፡
ሀገሪቱ ሚሳዔሉን ያስወነጨፈችው ሃዋሳል-1 አር ኤ-3 የተሰኘውን ስትራተጂካዊ የክሩዝ ሚሳኤል አቅምን እና አዲሱን ፒዮልጂ-1-2…
ተመድ በመካከለኛው ምስራቅ የሚስተዋለው አደገኛ የበቀል አዙሪት እንዲቆም አሳሰበ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን አደገኛ የበቀል አዙሪት ማስቆም አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አስገንዝበዋል።
የዋና ፀሐፊው ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በሰጡት መግለጫ፤ ዋና ፀሐፊው…
የኬንያ መከላከያ ሃይል ዋና አዛዥ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ መከላከያ ሃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦጎላ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡
የኬኒያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አደጋውን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራታቸውን የኬኒያ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በሰጡት ጋዜጣዊ…
የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም የተመድ አባልነት ጥያቄ ላይ ድምፅ ሊሰጥ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም የአባልነት ጥያቄ ላይ በነገው እለት ድምፅ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡
ከምክር ቤቱ 15 አባል ሀገራት ዘጠኙ ድምጽ የሚሰጡ ከሆነ እና ከአምስቱ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ካላቸው ሀገራት…