Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
ኢራን ከቻይና ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ እንደምታጠናክር ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ከቻይና ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ እንደምታጠናክር ተመራጩ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ገልጸዋል።
በቅርብ በታተመ መጣጥፋቸው ቻይና ከሩሲያ ጋር በመሆን በአስቸጋሪ ጊዜያት ከኢራን ጎን መቆሟን ያነሱት ፔዜሽኪያን÷ ይህንን ወዳጅነት…
በትራምፕ የፌስቡክና ኢንስታግራም ገጽ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነሳ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እና የአሁኑ እጩ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ የፌስቡክና ኢንስታግራም ገጽ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱ ተነገረ።
ሜታ ኩባንያ በትራምፕ የፌስቡክ እና የኢንስታግራም ገጾች ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ ያነሳው ትራምፕ…
የሩሲያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ የመንገደኞች አውሮፕላን በዋና ከተማው ሞስኮ አቅራቢያ በሚገኝ ደን ውስጥ መከስከሱ ተነገረ።
ሱኮይ ሱፐርጄት 100 የተሰኘው አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ጥገና ተደርጎለት መንገደኞችን ሳይጭን የሙከራ በረራ ሲያደረግ እንደነበር…
አሜሪካ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን በጀርመን ከተከለች ወታደራዊ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን በጀርመን የምትተክል ከሆነ ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወሰድ ሩሲያ አስጠነቀቀች፡፡
አሜሪካ ዘመናዊ የተባሉ ሚሳኤሎችን በፈረንጆቹ ከ2026 ጀምሮ በጀርመን እንደምትተክል ውሳኔ ያሳለፈችው በ75ኛው የሰሜን አትላንቲክ…
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በተኑ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከሁለት ባለስልጣናት ውጪ ካቢኔያቸው መበተኑን አስታውቀዋል፡፡
ውሳኔው የተለያዩ የግብር ጭማሪዎችን በያዘው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግ ላይ የተከሰተውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ የተወሰነ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
በዚህ…
በህንድ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ጉዳት ደረሰባቸው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ህንድ በተከሰተ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነገረ፡፡
አደጋው በኡታር ፕራዴሽ ግዛት የፍጥነት መንገድ ላይ ተደራራቢ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከወተት ጫኝ ተሸከርካሪ ጋር…
ሂዝቦላህ በእስራኤል የጦር ካምፖች ላይ ጥቃት መፈፀሙን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰው የሂዝቦላህ ቡድን በእስራኤል የጦር ካምፖች ላይ መጠነ ሰፊ የአፀፋ ጥቃት መፈፀሙን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አደረገ፡፡
ቡድኑ በሳምንቱ መጨረሻ በሰሜናዊ እስራኤል በሚገኙ ሶስት የጦር ሰፈሮች ላይ የአፀፋ ጥቃት መፈጸሙን…
ብሪክስ ራሱን የቻለ የፋይናንስ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪክስ ራሱን የቻለ የፋይናንስ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን ሩሲያ አስታወቀች፡፡
በቻይና ቤጂንግ በተካሄደው 12ኛው የዓለም የሰላም ፎረም ላይ፥ ሩሲያ ከብሪክስ ሀገራት ጋር በብሔራዊ ምንዛሬ የምታደርገው የንግድ ልውውጥ መጠን በየጊዜው እያደገ መሆኑ…
ማሱድ ፔዜሽኪያን የኢራን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የለውጥ አቀንቃኙ ዶክተር ማሱድ ፔዜሽኪያን ተፎካካሪያቸውን ወግ አጥባቂውን ሳኢድ ጃሊሊን በማሸነፍ የኢራን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።
በምርጫው በተሰጠው ድምጽ ዶክተር ፔዜሽኪያን 53 ነጥብ 3 በመቶ ሲያገኙ፤ ተፎካካሪያቸው ጃሊሊ 44 ነጥብ 3 በመቶ…
25 ሰዎች ከሱዳን ግጭት ሸሽተው በባህር ሲጓዙ ሰጥመው ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ሱዳን ሲናር ግዛት ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ግጭት ሲሸሹ የተሳፈሩበት የእንጨት ጀልባ ተገልብጣ ቢያንስ 25 ሰዎች በባህር ሰጥመው ህይወታቸው እንዳለፈ ተነግሯል።
የአስቸኳይ ድጋፍ ሰጪ ኃይል ወደ አካባቢው ሲገባ፣ ከአቡ ሁጃር ከተማ…