Fana: At a Speed of Life!

ኢዜአ እና ቲቪ ብሪክስ ኢንተርናሽናል ሚዲያ ኔትዎርክ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) እና የቲቪ ብሪክስ ኢንተርናሽናል ሚዲያ ኔትዎርክ በጋራ መስራት የሚያስችለውን የትብብር መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። በበይነ መረብ በተደረገው የስምምነት ፊርማ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2017 በጀት 37 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2017 በጀት ከ37 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ ፀድቋል። የክልሉ ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የ2017 ዓ.ም በቀረበው ረቂቅ በጀት ላይ ከተወያየ…

የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ፈቃድ መስጠት የሚያስችል መመሪያ ወደ ትግበራ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ፈቃድ መስጠት የሚያስችል መመሪያ በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ወደ ትግበራ እንዲገባ ተደረገ፡፡ ባለሥልጣኑ ለሰነደ ሙዓለ ንዋዮች፣ ለተዛማጅ ውሎችና ለያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ…

ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በራሳቸውን ገንዘብ ለመገበያየት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ለግብይት የራሳቸውን ገንዘብ ለመጠቀም ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ ፥ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ብሔራዊ ባንክ ገዢ…

ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የውጭ ባለሃብቶችን እየሳበች ነው – አምባሳደር ፈይሰል አልይ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የውጭ ባለሃብቶችን እየሳበች ነው ሲሉ በኳታር፣ የመን እና ኢራን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፈይሰል አልይ ገለጹ፡፡ አምባሳደር ፈይሰል፥ በኳታር ከሚገኘው ኮን ግሩፕ ጋር በንግድ፣…

ናይጄሪያዊው ቱጃር አሊኮ ዳንጎቴ ከሀገሬ ውጭ ቤት የለኝም አሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጄሪያዊው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ ከሀገሬ ውጪ ቤት የለኝም ሲሉ በመግለጽ ብዙሃኑን የሀገራቸውን ዜጎች አስገርመዋል። ዳንጎቴ በትውልድ ከተማቸው ካኖ እንዲሁም በሌጎስ ካሏቸው ሁለት ቤቶች በስተቀር የመኖሪያ ቤት እንደሌላቸው ገልጸው፤ ወደ ሀገሪቱ…

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሳተፍ የሚፈልጉ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በበይነ መረብ የሚመዘገቡበት ሁኔታ ተመቻቸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች መሳተፍ ለሚፈልጉ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በበይነ መረብ መመዝገብ የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸቱን ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በበጎ ፈቃድ መርሐ-ግብሮች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንም…

በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 14 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው በተባለ ቦታ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሥድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ በተጨማሪም በ14 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡ አደጋው የተከሰተው በሁለት መኪኖች ግጭት መሆኑም ነው የተመላከተው፡፡

964 ኩንታል ማዳበሪያ በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተያዙ 5 ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ስም ሀሰተኛ የወጪ ደረሰኝ በመጠቀም 964 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተያዙ አምስት ግለሰቦች በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ወንጀል ችሎት…

ከግድያ ሙከራው በኋላ ትራምፕ በደጋፊዎቻቸው የጀግና አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሣምንቱ መጨረሻ በግድያ ሙከራ ከቆሰሉ በኋላ የቀኝ ጆሯቸው ታሽጎ ወደ ሪፐብሊካን ብሔራዊ ኮንቬንሽን አዳራሽ ሲገቡ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል። መደበኛውን የሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩነት በማሸነፍ…