Fana: At a Speed of Life!

ከሕገ ወጥ ግንባታ ጋር ተያይዞ 12ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ የደንብ አስከባሪዎች ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕገ ወጥ ግንባታ ማስቆም ሲገባቸው 12 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ አምስት የደንብ አስከባሪዎች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ። የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የጸረ ሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው፡፡…

የዐባይ ሀገራት በዐባይ ውሃ ሀብት የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ስምምነት መድረስ አለባቸው – ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓባይ ሀገራት በዐባይ ውሃ ሀብት የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ስምምነት መድረስ እንደሚገባቸው የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትሩ በኬኒያ ናይሮቢ ለ17ተኛ ጊዜ እየተከበረ በሚገኘው የዓባይ ቀን ኢትዮጵያን በመወከል…

በመዲናዋ ሠራተኞች ወድቀው ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የሕንጻው ግንባታ ፈቃድ ታገደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ትናንት በግንባታ ላይ ከነበረ ሕንጻ ሦስት ሠራተኞች ወድቀው ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ዛሬ የሕንጻው የግንባታ ፈቃድ ታግዷል፡፡ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በግንባታ ላይ ከነበረ ሕንጻ ላይ ሦስት የቀን ሠራተኞች…

“ሜድ ኢን ጀርመን-አፍሪካ” የንግድ ዓውደ-ርዕይ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ “ሜድ ኢን ጀርመን-አፍሪካ” የተሠኘ የንግድ ዓውደ-ርዕይ እንደምታስተናግድ ተገለጸ፡፡ የንግድ ዓውደ-ርዕዩ ከፈረንጆቹ መጋቢት 2 ቀን ጀምሮ እስከ 4 እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡ ኢትዮጵያ የምታስተናግደው ዓውደ-ርዕይ የአፍሪካ ሀገራትን ኢንዱስትሪዎች ከሌሎች ሀገራት የንግድ አጋሮች…

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 6 ወራት ለ2 ሺህ 250 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሥድሥት ወራት ለ2 ሺህ 250 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ለታ አበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ባለሃብቶች…

የገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋር ቡድን አባላት ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋር ቡድን አባላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ ውይይቱን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ናቸው። በውይይቱ በኢትዮጵያ…

ኔቶ ለዩክሬን የጦር ጀቶች እንዳይቀርቡ ከለከለ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሀገራት ለዩክሬን የጦር ጄቶች እንዳይቀርቡ ውሳኔ ማሳለፋቸው ተገለጸ፡፡ ምንም እንኳን ኪየቭ ምዕራባውያኑ ወዳጆቿን ደጋግማ ዘመናዊ የጦር ጀቶች እንዲልኩላት ብትወተውትም ሰሚ ጆሮ…

አምራች ኢንዱስትሪውን በፋይናንስ በመደገፍ ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል- አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአምራች ኢንዱስትሪው የፋይናንስ ድጋፍ በመስጠት ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የፋይናንስ ተቋማት አምራች ኢንዱስትሪውን በፋይናንስ እንዲደግፉ ያለመ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር…

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ስኬታማና ኢትዮጵያ አቅሟን ያሳየችበት ነው -አምባሳደር መለስ ዓለም

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ስኬታማና ኢትዮጵያ አቅሟን ያሳየችበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ገለፁ፡፡ አምባሳደር መለስ ዓለም በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ እንዳሉት፥ በጉባኤው 29 የሀገራት መሪዎችና 53…

ለሊሴ ነሜ በቻይና ንግድ ሚኒስቴር የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጄንሲ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በቻይና ንግድ ሚኒስቴር የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኤጄንሲ ዳይሬክተር ሊዩ ዲያንክሰን ጋር ተወያዩ። በውይይታቸውም በተቋማቱ መካከል ያለውን ትብብር በኢንቨስትመንት አጋርነት እና…