Fana: At a Speed of Life!

በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ሥራዎችን ወደላቀ ውጤት ለማሸጋገር እየተሠራ ነው- አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ሥራዎችን ወደላቀ ውጤት ለማሸጋገር እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ። የክልሉ የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል፡፡…

ኢትዮጵያ ጸንታ የቆመችው ሕይወታቸውን ሳይሰስቱ የሚሰጡ ጀግኖች ስላሏት ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ጸንታ የቆመችው ሕይወታቸውን ሳይሰስቱ የሚሰጡ ጀግኖች ልጆች ስላሏት ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በፖሊሳዊ አገልግሎት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላት የዕውቅናና…

የአፍሪካን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ትክክለኛው አቅጣጫ አፍሪካዊ መፍትሔ ነው- አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፍሪካን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ትክክለኛው አቅጣጫ አፍሪካዊ መፍትሔ መስጠት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ተናገሩ፡፡ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ወጣቶች ጉባኤ ላይ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚል…

የትግራይ ሕዝብ ሕወሓት ከጫነበት ቀንበር ነጻ እንዲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መሥዋዕትነት እየከፈለ ነው – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የትግራይ ሕዝብ ሕወሓት ከጫነበት ቀንበር ነጻ እንዲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መሥዋዕትነት እየከፈለ ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የመከላከያ ሰራዊቱ መሥዋዕትነት የታሰበውን ግብ እንዲያሳካ የትግራይ ሕዝብ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የመከላከያ ሠራዊቱን…

የኢፌዲሪ መንግሥት በሴዑል በዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ ኮሪያ ሴዑል ዓመታዊ በዓል በማክበር ላይ በነበሩ ዜጎች በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የሰው ህይወት በመጥፋቱ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡ በየዓመቱ በሚከበረው “ሃሎዊን” በዓል በደረሰው የመገፋፋት አደጋ በርካቶች ለሞት…

ከሰሜን ወሎና አካባቢው በአሸባሪው ህወሓት ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአላማጣ፣ ቆቦ፣ ዋጃ እና ባላ እንዲሁም ከሌሎች አካባቢዎች በአሸባሪው ህወሓት ተፈናቅለው በጃራ መጠለያ ካምፕ የነበሩ 30 ሺህ 400 ወገኖች ወደ ቀያቸው መመለስ ጀምረዋል፡፡ ሃብትና ንብረታቸው በሽብር ቡድኑ በመዘረፉ መንግሥት ቀጣይነት ያለው…

መንግስት ነፃ በወጡ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ነፃ በወጡ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፍና የህክምና መድሃኒት ማቅረብ ጀመረ፡፡ የፊደራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም እንደገለፁት፥  መንግስት ከአሁን ቀደም ያደርግ የነበረውን…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሸገርን ማስዋብ ምዕራፍ ሁለት መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግንባታው የተጠናቀቀውን የሸገርን ማስዋብ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት መርቀው ከፈቱ። በምርቃ መርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የመዲናዋ የተለያዩ…