Fana: At a Speed of Life!

39ኛው የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባዔ በኬንያ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ልዩ የመሪዎች ጉባኤ በኬንያ እየተካሄደ ነው። በጉባዔው መሪዎቹ በአካባቢው ሀገራት የሚከሰተውን ድርቅ ማሸነፍ በሚቻልበት ሁኔታ፣ በሠላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ…

በሁሉም ከተሞች 196 ነጥብ 8  ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ ወይዘሮ  ጫልቱ ሳኒ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም ከተሞች 196 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ገለጹ፡፡ በ4ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር “ዐሻራችን ለከተሞቻችን” በሚል መሪ ቃል ሚኒስቴሩ ከለገጣፎ ለገዳዲ  ከተማ …

ጣሊያን በሰሜናዊ የሀገሪቷ ክፍል የድርቅ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን በሀገሪቷ ሰሜናዊ ክፍል በ70 ዓመታት ታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ በመመታቷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች፡፡ ድርቁ የተከሰተው ቀደም ሲል የሀገሪቷን አንድ ሦስተኛውን የግብርና ምርት አቅርቦት ይሸፍን በነበረው የ ”ፖ“ ወንዝ አካባቢ ነው…

ክልሎች ያዘዙትን የተሽከርካሪ ሰሌዳ በጊዜው ባለመውሰዳቸው የአሰራር ችግር ፈጥሮብኛል -የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ሰኔ 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ክልሎች ያዘዙትን የተሽከርካሪ ሰሌዳ በጊዜው ባለመውሰዳቸው የአሰራር ችግር ፈጥሮብኛል ሲል የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ገለፀ። የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዳሬክተር አቶ ስለሞን አምባቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷…

አሜሪካና ቻይና በንግድ ትስስርና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ማረጋጋት ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካና ቻይና በንግድ ትስስርና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ማረጋጋት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡ የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የለን እና የቻይና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሊው ሂ የባይደን አስተዳደር የዋጋ…

አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ “በብዙ ውጣ-ውረድ ውስጥ ሆነን ትልቅ ውጤት ማስመዝገብ ችለናል” አሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብዙ ውጣ-ውረድ ውስጥ ሆነንም ቢሆን ትልቅ ውጤት ማስመዝገብ ችለናል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የምክር ቤቱን የአፈጻጸም ደረጃ አመላከቱ፡፡ የምክር ቤቱ አማካሪ እና አስተባባሪ ኮሚቴዎች እንዲሁም የመንግስት ዋና እና…

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሐረማያ ኢፋ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤትን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የሐረማያ ኢፋ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤትን መርቀው ሥራ አስጀመሩ። በ274 ሚሊየን ብር የተገነባው አዳሪ ትምህርት ቤቱ የተማሪዎች መማሪያን ጨምሮ የአስተዳደር እና…

ተጨማሪ ጥቃትና ጭፍጨፋ እንዳይከሰት በተጋላጭ መንደሮች የሚሊሻና የኮሙኒቲ ፖሊሲንግ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወገኖቻችን ላይ ተጨማሪ ጥቃትና ጭፍጨፋ እንዳይከሰት ሁሉንም ተጋላጭ ቀበሌዎች እና መንደሮችን በመለየት አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው እንዲሁም ነዋሪው ራሱን በተደራጀ መልኩ እንዲከላከል የሚሊሻና የኮሙኒቲ ፖሊሲንግ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አል ቡርሐን ጋር በናይሮቢ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አዱልፈታህ አል ቡርሐን ጋር በናይሮቢ ተወያዩ። ለኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ናይሮቢ የሚገኙት መሪዎቹ፥ ከጉባኤው ጎን ለጎን በወቅታዊ…

በተለያዩ ክልሎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክልሎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል፡፡ በአማራ ክልል ከ359 ሺህ ለሚበልጡ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መስጠት መጀመሩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና…