Fana: At a Speed of Life!

ግምታቸው ከ9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ሲጋራዎችና ልባሽ ጨርቆች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን መተሓራ ከተማ ግምታቸው ከ9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ሲጋራዎችና ልባሽ ጨርቆች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዲቭዥን ሃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ ለኢዜአ…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት የቴሌኮም ምርት እና አገልግሎቶችን ለማቅረብ እና ለማከፋፈል ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ ለመሥራት ተፈራረሙ። ኢትዮ ቴሌኮም በመላው ኢትዮጵያ በ509 የራሱ የሽያጭ ማዕከል እንዲሁም በ134 የወኪል…

የሸዋል -ኢድ በዓልን አስመልክቶ ሐረርን ፅዱና ውብ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ነው- የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የሚከበረውን የሸዋል -ኢድ በዓል አስመልክቶ ከተማዋን ፅዱና ውብ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ፡፡ በከተማዋ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ደረቅ ቁሻሻ አስወጋጅና የአረንጓዴ አካባቢ…

በቤንች ሸኮ ዞን የወባ በሽታ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን የወባ በሽታ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኃይሌ ዘውዴ በሰጡት መግለጫ÷ በክልሉ በሶስት ዞኖች…

ዜጎች በፈለጉት አካባቢ ሀብትና ንብረት አፍርቶ የመኖር መብታቸው እንዲከበር የጋራ ሥራ ያስፈልጋል- የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአግላይነት አመለካከት ለሰላም መደፍረስ አንዱ ምክንያት በመሆኑ ዜጎች በሀገራቸው ውስጥ በፈለጉት አካባቢ ሀብትና ንብረት አፍርቶ የመኖር መብታቸው እንዲረጋገጥ ለማድረግ በጋራ መስራት እንደሚገባ የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ገለጸ፡፡…

ሶማሊያ በመጪው ሰኔ 15 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደምታካሂድ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶማሊያ ለረጅም ጊዜ የተራዘመውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሰኔ 15 እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡ የሶማሊያ ፓርላማ በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው፥ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሰኔ አጋማሽ የሚካሄድ ሲሆን፣ ከሁለቱም ምክር…

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ትናንት የመጨረሻ የኮቪድ-19 ታካሚን ወደ ቤት ሸኝቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ኮቪድ ታካሚ አድሯል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለሁለት አመታት ኮቪድ19 የተገኘባቸውን ህመምተኞች ተቀብሎ ሲያክም የቆየው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ትናንት የመጨረሻ ታካሚን ወደ ቤት ሸኝቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ኮቪድ 19 ታካሚ አድሯል። ቫይረሱ በኢትዮጵያ ከተገኘ በኋላ ሆስፒታሉ ላለፉት…

የምርምር ተቋማት በውሃ ዲፕሎማሲና ተግባቦት ላይ በመስራት የኢትዮጵያን ጥቅም ማስከበር አለባቸው- የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርምር ተቋማት በውሃ ዲፕሎማሲና ተግባቦት ላይ በትኩረት በመስራት ለኢትዮጵያ ጥቅም መከበር ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ገለጹ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ፣ የውሃ ዲፕሎማሲ እና…

በማጃንግ ዞን በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ ከ3 ሺህ 800 ሄክታር በላይ ሰብል ላይ ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ሰሞኑን በረዶ እና ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ምክንያት ከ3 ሺህ 800 ሄክታር በላይ ሰብል ጉዳት መድረሱን ተገለጸ፡፡ የጎደሬ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ይስሀቅ አብርሀም በረዶ እና ንፋስ…

በመዲናዋ ከዛሬ ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ይሰጣል ፡፡ የክትባት ዘመቻው ከዛሬ ሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን÷ ቤት ለቤት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡ በዚሁ…