Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የመጥፋት አደጋ የተደቀነባቸው ቋንቋዎችን ለማበልጸግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጥፋት አደጋ ስጋት የተደቀነባቸውን ቋንቋዎች በመለየት የመሰነድና እንዳይጠፉ የማበልጸግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ አስታወቀ። አካዳሚው 50ኛ ዓመት የጥናትና ምርምር ጉዞውን የሚዘክር ክብረ-በዓል…

977 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) 977 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ 977 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው…

በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የፖሊሲ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የፖሊሲ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አስታውቋል።   የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን አገራዊ ፋይዳ ያለው ዘላቂ ተግባር አድርጎ ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት…

ከፍተኛ የክረምት ዝናብ በሚያገኙ አካባቢዎች ጥንቃቄ እንዲደረግ ግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ክረምት ወቅት ከፍተኛ ዝናብ በሚያገኙ አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን ከወዲሁ በማዘጋጀት ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የግብርና ሚኒስቴር አሳስቧል። ሚኒስቴሩ ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሚወጡ  ትንበያዎችን…

ኢዜአ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ሁለት ሺህ መጻህፍት አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) በሁለተኛ ዙር ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ሁለት ሺህ መጻህፍት አበረከተ፡፡ ድርጅቱ በሀገር አቀፍ ካሉት 38 ቅርንጫፍ ጣቢያዎች እና ከግለሰቦች ያሰባሰባቸውን የተለያዩ ይዘት ያላቸው መጻህፍትን ነው ለአብርሆት ቤተ…

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ፥ የሥጋ ደዌ ተጠቂ የሆኑ የማህበረሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት እድሳት አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የሚኖሩ የስጋ ደዌ ተጠቂ ማህበረሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት እድሳት በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከክረምት በፊት ተጠናቀው የሚያልቁ…

በኢትዮጵያ 53 ቋንቋዎች የአጻጻፍ ስርዓት ተበጅቶላቸው ለመማር ማስተማር ውለዋል- ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ 53 ቋንቋዎች የአጻጻፍ ስርዓት ተበጅቶላቸው ለመማር ማስተማር መዋላቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ሁለተኛው አገር አቀፍ የቋንቋዎች ትርጉምና አስተርጓሚነት ጉባኤ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ…

ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የሩዋንዳ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ዳንኤል ኔሚጄ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒዬም ኮሌጅን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም የሆስፒታሉን የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥና እና የሕክምና ትምህርት…

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በሶማሌ ክልል ለ1 ሺህ አባወራዎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት በሶማሌ ክልል ቱሊጉሌድ ወረዳ ለ1 ሺህ አባወራዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉ የበቆሎንና የማሽላ ዘርን የሚያካትት ሲሆን÷ በክልሉ ላሉ 4 ሺህ አባወራዎችም የስንዴ ስርጭት በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ…

ወጣቱን ኃይል ሊያሳጣን የሚችለውን ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ልንከላከለው ይገባል – ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራቹን የወጣት ኃይል ጉዳት ላይ ሊጥል የሚችለውን ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ለነገ ሳንል ልንከላከለው ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ተናገሩ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በሰዎች የመነገድና በሕገ…