Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን የማዳን ጥሪውን ተከትሎ እየተመመ ያለው ህዝብ ያሳየው ምላሽ በእጅጉ የሚደነቅ ነው- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን የማዳን ጥሪውን ተቀብሎ እየተመመ ያለው የህዝብ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ በቁርጥ ቀን ልጆቿ ተጋድሎ የጥፋት ኃይሎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር ያላትን ዝግጁነትና ተግባር የሚያመለክት መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡…

በመዲናዋ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ የጦር መሳሪያ ያላቸው ግለሰቦች ምዝገባ እያካሄዱ ነው-ዶ/ር ቀነዓ ያደታ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የጦር መሳሪያ ያላቸው ግለሰቦች ምዝገባ እያካሄዱ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ገለጹ። የመዲናዋ ነዋሪዎች ከጸጥታ…

የኦሮሚያ ክልል የአርሶ አደሩ ምርት በቀጥታ ለሸማቹ እንዲደርስ እየሠራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የአርሶ አደሩን የግብርና ምርት በቀጥታ ለአዲስ አበባ ሸማቾች ለማቅረብ እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡ የተፈጠረው ምህዳር ÷ ለኦሮሚያ ክልል አርሶ አደሮች የገበያ ትስስር…

ኃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆችንና ‘ማህበራዊ አንቂ ነን’ የሚሉ ግለሰቦችን እንደማይታገስ መንግስት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ኃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እና ‘ማህበራዊ አንቂ ነን’ የሚሉ ግለሰቦችን እንደማይታገስ መንግስት አስታውቋል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው መግለጫ መንግስት ያቀረበውን ሀገርን የመታደግ ጥሪ…

የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለነበሩ ተማሪዎች ጊዜያዊ ምደባ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር በመቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ ራያ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ ለነበሩ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ምደባ አካሄደ። ሚኒስቴሩ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ ተማሪዎቹ የተመደቡባቸውን ከፍተኛ…

ከህወሓት እና ሸኔ ጋር ግንኙነት የነበራቸው 98 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 98 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ እንደገለጹት÷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመውጣቱ አስቀድሞ…

በቤኒሻንጉል ለተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የስራ ስምሪት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ለባለድርሻ አካላት በዛሬው ዕለት ማብራሪያ እና የስራ ስምሪት ተሰጥቷል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን፣ በአገር ደረጃ የታወጀውን የአስቸኳይ…

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ህወሓት እየፈፀመ ያለውን ሽብር ሊያወግዝ ይገባል – አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከዴንማርክ አምባሳደር ኪራ ስሚዝ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ላጋጠማት ችግር ዋና ተጠያቂው ህወሓት መሆኑን…

ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው፡፡ ማብራሪያውን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና በፍትህ ሚንስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እየሰጡ ነው።…

ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ የጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጸጉረ ልውጦችን በመለየት ለአካባቢያችን ሰላም በትኩረት በመሥራት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚነት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ሲሉ የጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ነዋሪዎቹ÷ አሁን ላይ በሀገሪቱ ከተጋረጠው አደጋ…