Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ወለጋ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ወለጋ፣ ነጆ ከተማ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች ተይዘዋል። ከዚህም ጋርተያይዞ ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡ ተተኳሽ ጥይቶቹን የጫነው አይሱዙ መኪና ታርጋ ቁጥሩ AA 32684 ሲሆን÷ በቁጥጥር ስር…

27ኛው የኢትዮ-ጂቡቲ የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች እና ኮሚሽነሮች ስብሰባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 27 ኛው የኢትዮ-ጂቡቲ የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች እና ኮሚሽነሮች ስብሰባ በአርታ ጂቡቲ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው÷ የሁለቱ ሃገራት ህዝቦች የጋራ ዕጣ ፈንታ እና የጋራ…

437 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ 84 ህጻናትን ጨምሮ 437 ዜጎች ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ፡፡ ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል እንዳደረጉላቸው…

በትምህርት ልማት ዘርፍ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ልማት ዘርፉ የኮሮና ቫይረስ ፣ የጸጥታ እና የፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ ሆኖ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ፡፡ በዚህም የፖሊሲ ለውጦችን በማድረግ የቅድመ አንደኛ ደረጃ በሁለት ዓመት እንዲጠናቀቅ፣ መካከለኛ ደረጃ ከ 7ኛ እስከ…

በጉጂ ዞን 2 ሺህ 858 የክላሽ እና ብሬን ጥይቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉጂ ዞን፣ ጎሮ ዶላ ወረዳ፣ ቢታታ ቀበሌ ሠላም ለማደፍረስ ተግባር ሊውሉ የነበሩ 2 ሺህ 858 የክላሽ እና ብሬን ጥይቶች ተይዘዋል፡፡ ለዕኩይ ዓላማ ሊውሉ የነበሩት ተተኳሽ ጥይቶች፣ ታርጋ ቁጥሩ 35819A.A በሆነ የአይሱዙ መኪና ተጭነው፥…

የሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የሴካፋ ሻምፕዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታውን ዛሬ ያካሂዳል፡፡ መርሃ ግብሩ እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግርኳስ ቡድን ከኡጋንዳው አቻው ሌዲ ዶቭስ ኤፍሲ ጋር…

በማይጠብሪ ግንባር ከተለያዩ አካባቢዎች የሚቀርበው ድጋፍ ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጎንደር ከተማ የሚኖሩ ባለሀብቶች፣ ነጋዴዎችና የሲቪክ ማህበራት ማይጠብሪ ግንባር ለተሰለፈው ሠራዊት ግንባር ድረስ በመገኘት የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል። የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ሲሳይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷…

አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት ዘርፉን ያዘምናል

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ ፍኖተ ካርታ የትምህርት ጥራትንን የሚያረጋግጥ፣ የትምህርት ስርዓቱ ከኢኮኖሚው ጋር እንዲጣጣምና ዘርፉ በቴክኖሎጂ እንዲዘምን የሚያደርግ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።   አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ከዚህ…

የካፋ ዞን 223 ሰንጋዎችን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፋ ዞን 223 ሰንጋዎችን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉን የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ሃላፊ አቶ መስፍን ተስፋዬ እንደገለጹት÷ከዞኑ ለመከላከያ ሰራዊት በድጋፍ የተበረከቱት ሰንጋዎች ከሁሉም…

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊ ከታሊባን አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ አፍጋኒስተን ገብተዋል፡፡ ማርቲን ግሪፍትስ ወደ አፍጋኒስታን ቀኑት ከታሊባን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ…