Fana: At a Speed of Life!

ከሀዲውን ኮሎኔል በቁጥጥር ስር ያዋለችው ጀግናዋ ም/አስር አለቃ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 20ኛ ቃሉ ክፍለ ጦር ሰሜን ዕዝ ካሏት የጦር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ክፍለ ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው ምክትል አስር አለቃ ገባያነሽ ደባልቄ የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ አጃቢ ነች ። ጁንታ መሆኑን ግን…

ተጨማሪ 430 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 150 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 4 ሺህ 298 የላቦራቶሪ ምርመራ 430 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ። በአጠቃላይ እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 110 ሺህ 984 ደርሷል።…

የፌደራል ፖሊስ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን መቐለ ገባ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን መቐለ ከተማ መግባቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። መቐለ የገባው ቡድን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት የጁንታውን ተፈላጊ ወንጀለኛ ቡድን ማደን ጀምሯል ተብሏል።…

ሩሲያ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ለማክበር ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ተረጋግጧል- ሚኒስትሮቹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ውይይት አድርገዋል። በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ እና ሩሲያን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት በተመለከተ ሚኒስትሮቹ ውይይት አድርገዋል።…

መቐለ ከተማ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ወደ እንቅስቃሴ እየተመለሰች ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊቱ ቁጥጥር ስር በዋለችው መቐለ ከተማ በተወሰነ መልኩም ቢሆን የሰዎች እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ የጋዜጠኞች ቡድን በዛሬው ዕለት በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች ቅኝት አድርጓል። በዚህም በተወሰነ ደረጃ እንቅስቃሴ…

በመቐለ ከተማ በተደረገ ብርበራ የጥፋት ቡድኑ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ዴፖ ተይዟል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቐለ ከተማ የጥፋት ሃይሉን አባላትና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል የቤት ለቤት ፍተሻ ተጀምሯል፡፡ በዚህም በከተማው የጥፋት ቡድኑ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ዴፖ በብርበራ በሰራዊቱ ተይዟል፡፡ በወቅቱም ሶስት ኮንቴነር ጠመንጃ፣…

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ወንጀል የተከሰሱት ጥላሁን ያሚን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ላይ የዐቃቤ ህግ ምስክር መሰማት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ወንጀል የተከሰሱት ጥላሁን ያሚን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ላይ የዐቃቤ ህግ ምስክር መሰማት ተጀመረ፡፡ በዛሬው ዕለት ዐቃቤ ህግ 12 ምስክሮችን ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የሦስቱ ተሰምቷል፡፡ በተጨማሪም ሌላ…

አቶ ደመቀ መኮንን በ21ኛው አፍሪካ ሕብረት ልዩ የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተካፈሉ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 23 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው በ21ኛው አፍሪካ ሕብረት ልዩ የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተካፍለዋል። ስብሰባው በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና ትግበራ እና…

መንግስት በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየሰራ ነው – ወ/ሮ ሙፈሪያት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ። “ወደ ሱዳን የተሰደዱ ንጹሃን ዜጎችን የመመለስና የማቋቋም ስራ ይሰራል” ብለዋል።…