Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ከ640 ሺህ በላይ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ640 ሺህ በላይ ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ገለፀ። በቢሮው የመጠጥ ውሀ አቅርቦት ዳይሬክተር አቶ ታጠረ…

በህዳሴ ግድብ  ዓሳ የማምረት ስራ በስፋት እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በሌሎችም የሀገሪቷ አካባቢዎች ዓሳ የማምረት ስራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ገለጹ። ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) እንዳሉት÷መንግስት ሀገሪቷ ጥራትና…

ዶናልድ ትራምፕ በቲክቶክ ላይ የተላለፈው ውሳኔ እንዲዘገይ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክቶክ ለአሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት ነው በሚል እንዲሸጥ ካልሆነም እንዲዘጋ የተላለፈው ውሳኔ እንዲዘገይ መጠየቃቸው ተሰማ። የአሜሪካ መንግስት የቲክቶክ እናት ኩባንያ የሆነውን…

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መካሄድ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መካሄድ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷"ዛሬ ጠዋት እየተከናዋኑ ባሉ ጥረቶች ላይ ለመወያየት የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ…

የቅዱስ ገብርዔል ዓመታዊ የንግስ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታሕሣሥ 19 የሚከበረው የቁልቢ እና የሐዋሳ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ዓመታዊው ክብረ በዓሉ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ነው በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች  በደመቀ ሁኔታ…

ዛሬ አመሻሽ ላይ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አመሻሽ 12 ሠዓት ከ26 ላይ በፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ በተደጋጋሚ እየተስተዋለ መሆኑንም ነው በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና…

310 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 310 ኢትዮጵያውያን ባለፉት 15 ቀናት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ለተመላሽ ወገኖች ድጋፍ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ…

የአዘርባጃን አውሮፕላን አደጋ የተከሰከሰው “በውጫዊ ጣልቃ ገብነት ነው” ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዘርባጃን አየር መንገድ በካዛኪስታን የተከሰተው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ መንስዔ “ከውጭ የተፈጸመ አካላዊ እና ቴክኒካዊ ጣልቃ ገብነት ነው” ብሏል፡፡ አውሮፕላኑ ከውጭ የመጣ ጣልቃ ገብነት ከገጠመው በኋላ መከስከሱን አየር መንገዱ ገልጿል…

በአማራ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማሕበረሰቡ ለመቀላቀል ያለመ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከአማራ ክልል መንግሥት ጋር በክልሉ ያሉ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማሕበረሰቡ መቀላቀልና መልሶ ማቋቋም በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ምክክር አካሂዷል። ለአተገባበር እንዲረዳም የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ዕቅድ፣ የፕሮግራም ይዘት፣…

የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ለዓይነ ስውራን የመነፅር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በደብረ ብርሃን ከተማ ለ250 ዓይነ ስውራን ዘመናዊ የማንበቢያ መነፅር ድጋፍ አድርጓል። በድጋፉ 113 ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን እና ቀሪዎቹ መምህራን እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች ናቸው ተብሏል፡፡ መነፅሩ…