የአድዋ ድል የህዝቦች የጋራ ውጤት በመሆኑ ለወቅታዊ የሀገሪቱ ችግሮች እንደ ምሳሌ ሊቀርብ ይገባል -ምሁራን
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአድዋ ድል የህዝቦች የጋራ ውጤት በመሆኑ ለወቅታዊ የሀገሪቱ ችግሮች እንደ ምሳሌ ሊቀርብ እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የታሪክ ምሁራን እንደገለጹት፥ ድሉ በአንድነትና በህብረት የተመዘገበ በመሆኑ…
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ም/ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንስ ቲመርማንስ ጋር ተወያዩ።
በቆይታቸውም የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የትብብር መስኮች ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል።…
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ለግብጹ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ ኤል ሲሲ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በራሳቸው እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ…
የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ሚኒስትር ስልክ ተጠለፈ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ሚኒስትር አያንዳ ድሎድሎ እና የምክትላቸው ስልክ መጠለፉ ተሰምቷል፡፡
የሃገሪቱ መርማሪዎች የደህንነት ሚኒስትሯ ስልክ እና የሌሎች ባርደረቦቻቸው ስልክ እንዴት እንደተጠለፈ በማጣራት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
መረጃ…
96 ኢትዮጵያውያን ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ 96 ኢትዮጵውያን በዛሬው ዕለት ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ተመላሾቹ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ እስር ቤቶች የቆዩ መሆናቸውን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።…
6 ሚሊየን ህፃናትን ከመቀንጨር ለመታደግ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነት ፕሮግራምን ውጤታማ በማድረግ በመቀንጨር የተጠቁ 6 ሚሊየን ህፃናትን ለመታደግ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
የሰቆጣ ቃል ኪዳን የሙከራ ምእራፍ ትግበራ የ2012 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ አመት አፈጻጸም ግምገማ በዋግኽምራ…
ETRSS-1 ሳተላይትን መቆጣጠርና መረጃ የመሰብሰብ ስራ በኢትዮጵያውያን እየተካሄደ መሆኑን ተገለፀ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ራሳቸውን ችለው ETRSS-1 ሳተላይትን የመቆጣጠርና መረጃዎችን የመሰብሰብ ስራ መስራት መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና…
በመዲናዋ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያትም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያትም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ ጨው በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ…