Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ የተከሰተውን ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ፡፡ ምክር ቤቱ የተከሰተውን የመሬት…

በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች መንግስታት ለከፍተኛ አመራሮች የሚሰጥ ስልጠና መርሐ ግብር ትውውቅ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች መንግስታት ለመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የሚሰጥ ስልጠና መርሐ ግብር ትውውቅ ተካሂዷል፡፡ የመርሐ ግብሩ ትውውቅ የተካሄደው ከ''አምስት ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ'' የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ጎን ለጎን ነው…

የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ለብሔራዊ ጥቅማቸው መከበር የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መደገፍ አለባቸው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ኢትዮጵያን ከመቃወም ይልቅ ለራሳቸው ብሔራዊ ጥቅም ሲሉ ኢትዮጵያን ቢደግፉ በብዙ ያተርፋሉ ሲል የቱርኩ የዜና ምንጭ ዴይሊ ሳባህ ገለጸ፡፡ የዜና ምንጩ ባስነበበው ጽሁፍ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ…

የሶማሌ ክልል ህዝብ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚ መሆን ችሏል-አቶ ሙስጠፌ መሐመድ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ህዝብ ላለፉት ስድስት የለውጥ ዓመታት ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚ መሆን መቻሉን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለፁ። በሶማሌ ክልል መንግስት በተመደበ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው 2ኛ ዙር የጅግጅጋ ከተማ…

የኦሮሚያ ክልል የሥራ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል የ2016 በጀት ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2017 ዕቅድ ውይይት መድረክ በአዳማ መካሄድ ጀምሯል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ…

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 17 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2017 በጀት ዓመት 17 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ። የቀረበው በጀት ከክልል ገቢ የሚሰበሰብ፣ ከፌዴራል መንግስት ድጎማና ከሌሎች የገቢ ምንጮች የሚገኝ መሆኑን ተገልጿል። በዚህም መሠረት ለክልል…

ብልጽግና ፓርቲ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ትናንት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት በሰው ሕይወት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡ ፓርቲው ባወጣው የሐዘን መግለጫ÷ በአደጋው…

በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉትን ለመደገፍ ሥራ መጀመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት በጎፋ ዞን ከተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተረፉና የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ ኮሚቴ በማቋቋም ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ጉዳት የደረሰባቸውና በሕይወት የተገኙ 10 ሰዎች…

ከኢትዮጵያ ጋር ያለኝ የልማት ትብብር ይቀጥላል- አየርላንድ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የልማት ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማሳደግ እንደምትሰራ የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሼል ማርቲን አረጋገጡ፡፡ በቅርቡ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የመጡት…