Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮ-ቴሌኮምን የተሞክሮ ማዕከል ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባውን የኢትዮ-ቴሌኮም የተሞክሮ ማዕከል ጎበኙ። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በአቶ ሽመልስ አብዲሳ ለተመራው ልዑክ ስለ ማዕከሉ ማብራሪያ…

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ደህንነት ዓለም አቀፍ ኦዲት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ደህንነት ዓለም አቀፍ ኦዲት በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡ በዓለም ዓቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት /አይሲኤኦ/ የኦዲት ባለሙያዎች የሚካሄደው ይህ ኦዲት ከ12 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ ነው። የብሔራዊ…

ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በልማት ሥራ ምክንያት በከፊል ዝግ እንደሚሆን ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በልማት ሥራ ምክንያት በከፊል ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በመንገድ ኮሪደር ልማት እና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስደው…

በዓረብ ሀገራት የሥራ ስምሪት ላይ ህገ-ወጥ ደላሎች አሁንም ዜጎችን ለኪሳራ እየዳረጉ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓረብ ሀገራት የሥራ ስምሪት ላይ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳትና ኪሳራ ለመከላከል እየተሰራ ቢሆንም ህገ-ወጥ ደላሎች አሁንም አሉታዊ ተጽዕኖ ማድረሳቸው እንዳልቆመ ተገለጸ። ዜጎች የተሻለ ገቢ ለማግኘት፣ ኑሯቸውን ለማሻሻልና ቤተሰባቸውን…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ቢሳው አቀና

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ቢሳው ጋር ለሚያደርገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ መዲናዋ ቢሳው ተጉዟል። 23 ተጫዋቾችን ያካተተው ልዑካን ቡድኑ ከአዲስ አበባ በቶጎ (ሎሜ) አድርጎ ቢሳው ከተማ ዛሬ ምሽት ላይ እንደሚደርስ ከኢትዮጵያ እግር…

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ለሜቻ ግርማ የዓመቱን የዓለም ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊድን በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት አትሌት ለሜቻ ግርማ የዓመቱን የዓለም ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸነፈ፡፡ በዚህም መሠረት በ3 ሺህ ሜትር መሠናክል የወንዶች ውድድር አትሌት ለሜቻ…

 የኢትዮጵያና የኮሪያ ሪፐብሊክ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚጠናከርበት ስምምነት ተደርጓል – አቶ አህመድ ሺዴ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና የኮሪያ ሪፐብሊክ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚጠናከርበት ስምምነት መደረጉን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ደቡብ…

የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል የህግ የበላይነትን በማስከበር፣ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ከጎበኙ በኋላ…

በማድሪድ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ጥሩነሽ ዲባባ 3ኛ ስትወጣ ዳዊት ወልዴ በቀደሚነት አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ማድሪድ በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር በሴቶች አንጋፋዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች። በወንዶች ደግሞ ዳዊት ወልዴ በቀዳሚነት አጠናቋል፡፡ ጥሩነሽ 10 ኪሎ ሜትሩን በ30 ደቂቃ ከ03 ሴኮንድ…

ኬልያን ምባፔ ሪያል ማድሪድን በይፋ ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኬልያን ምባፔ በነፃ ዝውውር ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሏል፡፡ ከፈረንሳዩ ክለብ ፓሪስ ሴን ዠርሜ (ፒ ኤ ሲ ጂ) ጋር ያለው ውል በፈረንጆቹ ሰኔ 30 2024 ላይ የሚያበቃው ምባፔ በአምስት ዓመት ኮንትራት ነው…