ኢትዮጵያ በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ባስመዘገበችው ድል ኤምባሲው ደስታውን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ባስመዘገበችው ድል በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደስታውን ገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ በደርባን በተካሄደው የቦክስ ውድድር ላይ ሦስት የብር እና ሦስት የነሐስ በድምሩ ስድስት ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡…