ስፓርት
በማድሪድ ትልቅ የቤት ሥራ የሚጠብቀው ዣቢ አሎንሶ….
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዣቢ አሎንሶ በሪያል ማድሪድ፣ በሊቨርፑል እንዲሁም ባየርን ሙኒክ ቤት በተጫዋችነት ዘመኑ ብቃቱን ያስመሰከረ ስኬታማ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ነበር፡፡
ከፈረንጆቹ 2009 እስከ 2014 ድረስም በሪያል ማድሪድ ቤት በተጫዋችነት አሳልፏል፡፡
በማድሪድ ቆይታው 236 ጨዋታዎችን በማድረግ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና የስፔን ላሊጋ ዋንጫን ጨምሮ በርካታ ዋንጫዎችን ከፍ አድርጓል፡፡
እንዲሁም ከእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል ጋር በፈረንጆቹ 2005 የውድድር ዓመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን…
Read More...
ባሕርዳር ከተማ በአርባ ምንጭ ከተማ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሕርዳር ከተማ በአርባ ምንጭ ከተማ 2 ለ 0 ተሸነንፏል፡፡
12 ሠዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ፤ የአርባ ምንጭን ግቦች አሕመድ ሁሴን በፍጹም ቅጣት ምት እና በጨዋታ አስቆጥሯል፡፡
የኮንፈረንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዙ ክለብ ቼልሲ ከስፔኑ ሪያል ቤቲስ ጋር የሚያደርጉት የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ላይ በፖላንድ ታርዚኒስኪ አሬና ስታዲየም ይደረጋል፡፡
በሪያል ቤቲስ በኩል በማንቼስተር ዩናይትድ ስኬታማ ጊዜ ያላሳለፈው እና በጥር የዝውውር መስኮት ቡድኑን የተቀላቀለው አንቶኒ እንዲሁም የሪያል ማድሪድ…
ኢትዮጵያ መድን ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሲዳማ ቡናን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡
የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች ወገኔ ገዛኸኝ፣ አቡበከር ሳኒ እና ብርሃኑ በቀለ (በራስ ላይ) ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ወደ ድል ሲመለስ ሲዳማ ቡና ከተከታታይ…
ሊቨርፑል ድሉን ከደጋፊዎቹ ጋር እያከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2024/25 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል ድሉን ከደጋፊዎቹ ጋር እያከበረ ይገኛል።
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በአንፊልድ ጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር ከደጋፊዎቹ ጋር 20ኛ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ድሉን እያከበረ ነው፡፡
በኮቪድ 19 ምክንያት ከአምስት ዓመት በፊት ሻምፒዮን ሆኖ…
የ2024/25 እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2024/25 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረጉ መርሐ ግብሮች ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡
ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ፣ ቼልሲ፣ አርሰናል እና ማንቼስተር ዩናይትድ ሲያሸንፉ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል ከክሪስታል ፓላስ ጋር አቻ ተለያይቷል።
ውጤቱን ተከትሎም ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል በ84 ነጥብ ሲያጠናቅቅ፤…
ዴቪድ ራያ እና ማትዝ ሰልስ የወርቅ ጓንት አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርሰናል ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ እና የኖቲንግሃም ፎረስት ግብ ጠባቂ ማትዝ ሰልስ የ2024/25 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዘመንን የወርቅ ጓንት በጋራ አሸንፈዋል።
ሁለቱ ግብ ጠባቂዎች በውድድር ዓመቱ 13 ጊዜ መረባቸውን ሳያስደፍሩ በመውጣት ነው የወርቅ ጓንቱን ማሸነፍ የቻሉት።
ከብሬንት ፎርድ በውሰት…