ስፓርት
አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በለንደን ማራቶን ትሳተፋለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 2023ቱ የለንደን ማራቶን የሴቶች ውድድር ትሳተፋለች፡፡
አትሌት ያለምዘርፍ ባለፈው ዓመት የተደረገውን የለንደን ማራቶንን ወድቃ በመነሳት በድንቅ ብቃት ማሸነፏ የሚታወስ ነው ።
የ21 ዓመቷ አትሌት 1 ሰአት ከ3 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ በሆነ ሰዓት የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን ባለቤት ስትሆን በ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ 29 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በመግባት የክብረወሰኑ ባለቤት ናት።
አትሌት ያለምዘርፍ ከኬንያዊቷ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ብሪጊድ ኮስጌ…
Read More...
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ2023ቱ የለንደን ማራቶን ይሳተፋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቀጣይ ሚያዚያ ወር ላይ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፍ ተገለፀ፡፡
ቀነኒሳ በቀለ በበርሊን ማራቶን 2 ሰአት ከ1 ሰከንድ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በማራቶን ታሪክ ሁለተኛው የፈጣን ሰዓት ባለቤት መሆኑ ይታወቃል ።
የሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ግማሽ ማራቶን…
ኤንዞ ፈርናንዴዝ የፕሪሚየር ሊጉ ውዱ ፈራሚ ሲሆን ማንቼስተር ዩናይትድ እና አርሰናል አማካይ አስፈርመዋል
አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች በጥር ወር የመጨረሻ ሰአታት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።
የእንግሊዙ ቼልሲ በ107 ሚሊየን ፓውንድ የቤኔፊካውን ኤንዞ ፈርናንዴዝ አስፈርሟል፡፡
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የ22 አመቱን አርጀንቲናዊ ለማስፈረም ለወራት ድርድር ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ትናንት ምሽት የተጫዋቹ ዝውውር ተጠናቋል፡፡…
በጀርመን በተካሄደ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን ካርልስሩህ በተካሄደ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በ3 ሺህ ሜትር በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አምስት ተከታትለው በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል፡፡
አትሌት ለምለም ኃይሉ 8 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ ከ55 ማይክሮ ሰከንድ…
ካፍ ለቻን ውድድር አሸናፊ የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት አሳደገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የቻን ውድድር አሸናፊ ለሚሆነው ሀገር የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት መጠን ማሳደጉን የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
የአፍሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሙትሴፔ እንደገለፁት ፌደሬሽኑ ለቻን አሸናፊ ሀገር የሚሰጠውን የገንዘብ ሽልማት 60 በመቶ መጨመሩን…
ለ44ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና አትሌቶች ልምምድ እያደረጉ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ የካቲት 18 ቀን 2023 በአውስትራሊያ ባትረስት ከተማ ለሚካሄደው 44ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ልምምድ እያደረጉ ነው፡፡
በውድድሩ ኢትዮጵያን የሚወክሉ 14 ወንድና 14 ሴት አትሌቶች ከነተጠባባቂዎቹ ከ40ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በወጣትና በአዋቂ ምድብ…
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተቋርጦ የሚጀመርበት ቀን ለአንድ ሣምንት ተራዘመ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ከተቋረጠበት የሚጀመርበት ቀን ለአንድ ሣምንት ተራዘመ፡፡
በአዳማ ከተማ የሚካሄደው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር መግለጹ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጅ ውድድሩ የሚጀመርበት ቀን ቀድሞ ከተገለፀው…