ስፓርት
በ2025 የዓለም የሰርከስ ውድድር ላይ ለሚሳተፈው ልዑክ ሽኝት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በ2025 የዓለም የሰርከስ ጥበብ ውድድር ላይ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ሽኝት አድርገዋል፡፡
ኢትዮ ዊንጌት ራሽያን ስዊንግ የተሰኘው የሰርከስ ቡድን ኢትዮጵያን በመወከል በሞስኮ በሚካሄደው የዓለም የሰርከስ አርት ውድድር ላይ ይሳተፋል፡፡
በዚህ ዓመት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ15 ሀገራት የተውጣጡ 200 የሰርከስ ጥበብ አርቲስቶች የሚሳተፉ ሲሆን፥ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ኢትዮጵያን ለሚወክሉ የሰርከስ ቡድን አባላት…
Read More...
ካርሎ አንቸሎቲ የአንድ ዓመት እስር ተፈረደባቸው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጣልያናዊው የሪያል ማድሪድ የቀድሞ አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ከገቢ ግብር ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
የወቅቱ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አንቸሎቲ በፈረንጆቹ 2014 በፈጸሙት የግብር ማጭበርበር ክስ የአንድ ዓመት እስር ቅጣት ተፈርዶባቸዋል፡፡
የ66 ዓመቱ ጣልያናዊ አሰልጣኝ ከሪያል ማድሪድ…
ከንግስና እስከ ባላንጣነት – የቀድሞው የፓሪስ ንጉስ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፓርክ ዴ ፕረንስ "ምባፔ ንጉሳችን፥ ኩራታችን ነህ" ተብሎ ቢዘመርለትም ወደ ማድሪድ መኮብለልን ሲመርጥ "ከእኛ ይልቅ ገንዘብን መርጠሃል" ተብሎ በራሳቸው በፒኤስጂ ደጋፊዎች ተብጠልጥሏል፡፡
በስተመጨረሻ ከክለቡ ፒኤሰጂ ጋር የመለያየቱ ነገር ቁርጥ ሲሆን በደጋፊዎች በክብር መሸኘቱ ይታወሳል፡፡
የተወደሰበትን የቀድሞ ክለቡን…
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በፍጻሜው ጨዋታ ስታዲየም ይገኛሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የክለቦች ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታን ለመታደም ስታዲየም ይገኛሉ፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሜት ላይፍ ስታዲየም በመገኘት የፍጻሜውን ጨዋታ እንደሚመለከቱ ዴይሊ ሜል ስፖርት ዘግቧል፡፡
በአዲስ አቀራረብ 32 ቡድኖችን አሳትፎ ውድድሩን የጀመረው የ2025 የክለቦች ዓለም ዋንጫ አሁን ላይ…
ኒውካስል ዩናይትድ አንቶኒ ኤላንጋን ለማስፈረም ተስማማ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኒውካስል ዩናይትድ ስዊድናዊውን የመስመር አጥቂ አንቶኒ ኤላንጋ ከኖቲንግሃም ፎረስት ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡
ኒውካስል ዩናይትድ ለተጫዋቹ ዝውውር 55 ሚሊየን ፓውንድ እንደሚከፍል ተነግሯል፡፡
የ23 ዓመቱ የቀድሞ የማንቼስተር ዩናይትድ ተጫዋች በኒውካስል ዩናይትድ የአምስት አመት ውል እንደሚፈርም…
ማርቲን ዙባሜንዲ አርሰናልን ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ስፔናዊው ኢንተርናሽናል ማርቲን ዙቢሜንዲ በይፋ መድፈኞቹን ተቀላቅሏል።
የ26 ዓመቱ ዙቢሜንዲ በ60 ሚሊየን ፓውንድ ነው ከስፔኑ ሪያል ሶሴዳድ የሰሜን ለንደኑን ክለብ የተቀላቀለው፡፡
በሪያል ሶሴዳድ ቤት ጠንካራ አቋሙን ማሳየት የቻለው ዙቢሜንዲ ለክለቡ በሁሉም ጨዋታዎች 236 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል።
ዙቢሜንዲ በቀጣዩ…
በ41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን አትሌት መሰረት ገብሬ እና ገመቹ ያደሳ አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በሴቶች መሰረት ገብሬ እና በወንዶች አትሌት ገመቹ ያደሳ አሸንፈዋል።
41ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ተካሂዷል።
በዚህም በወንዶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን በመወከል የተሳተፈው አትሌት ገመቹ ያደሳ አንደኛ…