ስፓርት
ኦሊጎነር ሶልሻየር የቤሽክታሽ አሰልጣኝ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ኦሊጎነር ሶልሻየር የቤሺክታሽ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ።
ሶልሻየር የቱርኩን እግር ኳስ ቡድን እስከ 2026 ለማሰልጠን መስማማቱን የተረጋገጡ የዝውውር መረጃዎችን የሚያወጣው ፋብሪዚዮ ሮማኖ በፌስ ቡክ ገፁ አስፍሯል።
ኦሊጎነ ሶልሻየር በማንቸስተር ዩናይትድ ከሁለት ዓመት ተኩል ስኬታማ የተጫዋችነት ዘመን በተጨማሪ እ.ኤ.አ ከ2019 እስከ 2021 በአሰልጣኝነት መርቷል።
Read More...
ድሬ ሀሪፍ ሀገር አቀፍ የብስክሌት ውድድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከታሕሣሥ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በድሬዳዋ ሲደረግ የቆየው ድሬ ሀሪፍ ሀገር አቀፍ የብስክሌት ውድድር የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ከአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ትግራይ እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ የተውጣጡ 36 የከፍተኛ ኮርስ ብስኪሌተኞች ተሳትፈዋል፡፡
80 ኪሎ ሜተር በሸፈነው የፍጻሜ ውድድር ዐቢይ…
የኤልክላሲኮ የፍፃሜ ጨዋታ በሳዑዲ አረቢያ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በስፔን ሱፐር ካፕ ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና (ኤልክላሲኮ) የሚያደርጉት የፍጻሜ ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጨዋታው በሳዑዲ ኪንግ አብዱላህ ስፖርት ሲቲ ስታዲየም ምሽት 4 ሰዓት ይደረጋል፡፡
በሱፐር ካፑ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና አትሌትክ ቢልባኦን እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ሪያል ሞዮርካን…
በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 10 ደረጃን በመያዝ አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ድል አስመዘገቡ።
ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ በዱባይ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያውያኑ የተሰጣቸውን ቅድሚያ ግምት አሳክተዋል።
በዚህም በሁለቱም ጾታ ከአንደኛ እስከ አስረኛ ድረስ ያለውን ደረጃ በመያዝ በፍጹም የበላይነት…
ሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ አንድ አቻ ተለያዩ፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ብሩክ በየነ ለሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ማርቲን ኪዛ ለፋሲል ከነማ ግቦቹን አስቆትረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና የሊጉን መሪነት ለመቻል…
መቻል ስሑል ሽረን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስሑል ሽረ በመቻል 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
የመቻልን ግቦች ሽመልስ በቀለ በ24ኛው እንዲሁም ግሩም ሀጎስ በ39ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የስሑል ሽረን የማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ አስቻለው ታመነ በ53ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ አስቆጥሯል፡፡
የዛሬው የመጨረሻ የጨዋታ መርሐ-ግብር…
መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 ረትቷል፡፡
የማሸነፊያዋን ግብም አዎት ኪዳኔ በ82ኛው ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡
በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የ13ኛ ሣምንት የዕለቱ መርሐ-ግብር ሲቀጥል÷ አዳማ ከተማ ከቅዱስ…