Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ባርሴሎና ኦሎምፒያኮስን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሦስተኛ ዙር መርሐ ግብር ባርሴሎና ኦሎምፒያኮስን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል፡፡ በጨዋታው ፈርሚን ሎፔዝ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ የሰራ ሲሆን፥ ማርከስ ራሽፎርድ (2) እንዲሁም ላሚን ያማል ቀሪዎቹን የባርሴሎና ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ በጨዋታው ኤል ካሀቢ ለኦሎምፒያኮስ ያስቆጠራት ግብ የግሪኩ ክለብ በዚህ የውድድር ዓመት በሻምፒየንስ ሊጉ ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች የተገኘች ብቸኛ ግብ ሆናለች፡፡ በሌላ ጨዋታ ካይራት አልማቲ ከፓፎስ…
Read More...

አሰልጣኝ ሲያን ዳይች የኖቲንግሃም ፎረስት አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ሲያን ዳይች የኖቲንግሃም ፎረስት አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡ አሰልጣኝ ሲያን ዳይች በኖቲንግሃም ፎረስት እሰከ ፈረንጆቹ 2027 ድረስ የሚያቆያቸውን ኮንትራት ተፈራርመዋል። አሰልጣኝ አንጂ ፖስቴኮግሉን ተክተው የኖቲንግሃም ፎረስት አሰልጣኝ የሆኑት ዳይች ፎረስት በዩሮፓ ሊግ ከፖርቶ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ስራቸውን…

አርሰናል ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ሌሎች የዛሬ ጨዋታዎች…

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሦስተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ዘጠኝ ጨዋታዎች በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ይደረጋሉ፡፡ በዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ባርሴሎና የግሪኩን ኦሎምፒያኮስ በሜዳው ሲያስተናግድ፥ የካዛኪስታኑ ካይራት አልማቲ ከቆጵሮሱ ፓፎስ ጋር ይጫወታሉ፡፡ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አርሰናል…

ባሕር ዳር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽረ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕር ዳር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽረ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ረትቷል። የባሕር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ክንዱ ባየልኝ፣…

በቶሮንቶ ዋተር ፍሮንት ማራቶን አትሌት ሹሬ ደምሴ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2025 ቶሮንቶ ዋተር ፍሮንት ማራቶን አትሌት ሹሬ ደምሴ አሸንፋለች። አትሌት ሹሬ ርቀቱን 2 ሰዓት 21 ደቂቃ ከ03 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት አልማዝ ከበደ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡ በወንዶች ምድብ አትሌት ወርቅነህ…

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስሎቬኒያ ሉብሊያ ማራቶን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በስሎቬኒያ ሉብሊያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡ በወንዶች በተደረገው ውድድር አትሌት ሃፍታሙ አባዲ 2 ሰዓት ከ 06 ደቂቃ ከ52 ሰኮንድ በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቋል። በውድድሩ ላይ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ከማል ሁሴን ሦስተኛ  ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሷል፡፡…

ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመጀመሪያ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል አቤል ያለው በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ ዳንላንድ ኢብራሂም የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጫዋች አቤል ያለው ላይ በሰራው ጥፋት…