Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የቀድሞ የሼፊልድ ዩናይትድ ተከላካይ ጆርጅ ባልዶክ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የሼፊልድ ዩናይትድ ተከላካይ እና አሁን ላይ ለግሪኩ ፓናቲናይኮስ በመጫወት ላይ የነበረው ጆርጅ ባልዶክ በ31 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ባልዶክ አቴንስ በሚገኘተው መኖሪያ ቤቱ መዋኛ ገንዳ ውስጥ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱ ተነግሯል፡፡ ፖሊስ የተጫዋቹን ሞት መንስኤ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጹን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል፡፡ ክለቡ ፓናቲናይኮስ በተጫዋቹ ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ ለቤተሰቡና አድናቂዎቹ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
Read More...

ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደቡብ ሱዳን ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣርያ ውድድር ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን 2 ለ 1 ተሸነፈች፡፡ ለደቡብ ሱዳን ግቦቹን ንጎንግ ጋራንግ እና ዳንኤል ቢቺኦክ ሲያስቆጥሩ÷ ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ዋንጫ ቱት ከመረብ አሳርፏል፡፡

በአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና የመጀመሪያ ቀን ውድድር ኢትዮጵያ 2 የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ እየተካሄደ በሚገኘው የ2024 የአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን ብስክሌተኞች ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡ ሜዳሊያዎቹ የተገኙት በጽጌ ካህሳይ እና ምዕራፍ ገ/እግዚአብሔር መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ኤሊዩድ ኪፕቾጌ በድጋሚ የዩኔስኮ የስፖርት አምባሳደር ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለት ጊዜ የኦሊፒክ ሻምፒዮኑ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የስፖርት አምባሳደር ሆኗል፡፡ ኬኒያዊው የማራቶን ባለታሪክ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ ለሁለት ዓመታት ነው የስፖርት አምባሳደር በመሆን የተሰየመው፡፡ የ39 ዓመቱ አትሌት በስፖርት ዘርፍ ላሳየው ዲሲፕሊን እና…

በሞሮኮ የእጅ ኳስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሶስት ክለቦች ትወከላለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሮኮ ላዩን ከተማ በሚካሄደው 45ኛው የአፍሪካ ክለቦች የወንዶች እና ሴቶች እጅ ኳስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሶስት ክለቦችን እንደምታሳትፍ ተገለፀ፡፡ በዚህም መሰረት መቻል፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ እጅ ኳስ ክለቦች በመድረኩ ኢትዮጵያን በመወከል ይሳተፋሉ። በወጣው ምድብ መሰረትም መቻል እጅ ኳስ…

የሊቨርፑል የቀድሞ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ወደ እግር ኳስ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው የቀድሞ የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በሬድቡል ኩባንያ ስር የሚገኙ የእግር ኳስ ክለቦች ሃላፊ መሆን የሚስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ በሬድ ቡል ኩባንያ ስር በዓለም አቀፍ ደረጃ የጀርመኑ ርቢ ሌብዢግ፣ የኦስትሪያው ሬድ ቡል ሳልዝበርግ፣ የአሜሪካው ኒውዮርክ ሬድ ቡልስ እና በብራዚል ደግሞ ሁለት እግር…

ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቼልሲው አማካይ ኮል ፓልመር የ2023/24 የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡ የ22 ዓመቱ ፓልመር በሕዝብ በተደረገ ምርጫ የሪያል ማድሪዱን ጁድ ቤሊንግሃም እና የአርሰናሉን ቡካዮ ሳካን በድምፅ በመብለጥ ነው ማሸነፍ የቻለው፡፡ ፓልመር ለሦስቱ አናብስቶች ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወተው…