Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

መቐለ 70 እንደርታ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ቀን 9 ሠዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቤንጃሚን ኮቴ የመቐለ 70 እንደርታ ማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል። ረፋድ 3 ሠዓት በተካሄደው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ስሑል ሽረን 5 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የዕለቱ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሠዓት ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ይገናኛሉ።
Read More...

ሐዋሳ ከተማ ስሑል ሽረን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ ስሑል ሽረን 5 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በጨዋታው ለሐዋሳ ከተማ አሊ ሱሌማን አራት ግቦችን ሲያስቆጥር ቀሪዋን አንድ ጎል ተባረክ ሄፋሞ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የሐዋሳ ከተማው የፊት መስመር ተጫዋች አሊ ሱሌማን በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች 19…

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ሱልጣን በርሄ፣ ናትናኤል ሰለሞን እና ዳዊት ገብሩ አስቆጥረዋል፡፡ ድሬዳዋ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ዘርዓይ ገብረሥላሴ ከመረብ…

አዳማ ከተማ ባሕር ዳር ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ባሕር ዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቢንያም አይተን እና ሙሴ ኪሮስ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ አዳማ ከተማ ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን ያሳካ ሲሆን÷በአንጻሩ ባሕር ዳር ከተማ ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎችን…

ኦስማን ዴምቤሌ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፈረንሳዊው የፒኤስጂ የፊት መስመር ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ የ2024/25 አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል፡፡ የ28 ዓመቱ ዴምቤሌ በውድድር ዓመቱ ባደረጋቸው 15 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች፤ 8 ጎል አስቆጥሮ 6 ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡ ፒኤስጂ በታሪኩ…

ማንቼስተር ዩናይትድ ማቲውስ ኩንሀን አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ማቲውስ ኩንሀን ከወልቭስ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡ የ26 ዓመቱ ማቲውስ ኩንሀ በማንቼስተር ዩናይትድ ቤት በፈረንጆቹ እስከ 2030 የሚያቆውን ውል ፈርሟል፡፡ ከአምሥት ዓመት ውሉ ባሻገር ለአንድ ዓመት የማራዘም ተጨማሪ አማራጭ መኖሩ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ…

ኢትዮጵያ ቡና የ100 ሺህ ብር ቅጣት ተጣለበት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጰያ ፕሪሚየር ሊግ 32ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ባጠፉት ጥፋት ክለቡ የ100 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበታል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ያደረገውን የ32ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ያለምንም ግብ…