ስፓርት
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የኢትዮ ኤሌክትሪክን ማሸነፊያ ግብ ከእረፍት መልስ ሀብታሙ ሸዋለም በ48ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በጨዋታው ማሸነፉን ተከትሎ 10 ነጥብ በመሰብሰብ ሊጉን በበላይነት መምራት ጀምሯል።
በሌላ በኩል የውድድር ዓመቱን ሁለተኛ ሽንፈት ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በአራት ነጥቦች 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ቀን 9 ሰዓት ላይ…
Read More...
በቻይና በተካሄደው የማራቶን ውደድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና በቤጂንግ እና ሆንዙ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
በሆንዙ የማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ሩቲ አጋ በ2:24:29 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን አሸንፋለች።
በወንዶች አትሌት ጫሉ ደሶ በ2:11:15 በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቋል።
በተመሳሳይ…
የኦሊምፒክ ስፖርት የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት ያስችላል – አቶ ቀጄላ መርዳሳ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሊምፒክ ስፖርት የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት ያስችላል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶች እና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፡፡
2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ ማጠቃለያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ…
ማንቼስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ማንቼስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት 30 በኢትሃድ ስታዲየም በሚካሄደው ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ባለፈው ሳምንት በአስቶንቪላ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ በሜዳው ይፋለማል፡፡
ሲቲዝኖቹ ባለፉት 9 የሊጉ ጨዋታዎች 16 ነጥብ…
ዩቬንቱስ – በተማሪዎች ተመስርቶ በስፖርቱ ዓለም የገነነ ስም
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከክርስቲያኖ ሮናልዶ እስከ ዚነዲን ዚዳን፣ ለሦስት ተከታታይ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ መሆን ከቻለው ሚሼል ፕላቲኒ እስከ አንድሪያ ፒርሎ እና ጂያንሉዊጂ ቡፎን በርካታ ከዋክብት የጣሊያኑን ገናና ክለብ ጥቁርና ነጭ ማልያ ለብሰው ተጫውተዋል፡፡
አሮጊቷ በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው የቱሪኑ ክለብ በጣሊያን ሴሪ አ 36 ዋንጫዎችን…
ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ሰባት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ምሽት 12:00 ላይ የሊጉ መሪ አርሰናል ወደ በተርፍ ሙር ስታዲየም ከበርንሌይ ጋር የሚጫወት ሲሆን፤ በተመሳሳይ ሰዓት ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር የሚጫወት ይሆናል።
እንዲሁም ብራይተን ሊድስ…
ኪሊያን ምባፔ የወርቅ ጫማ ሽልማቱን ተረከበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ የ2024/25 የውድድር ዘመን የወርቅ ጫማ ሽልማቱን በዛሬው ዕለት ተረክቧል፡፡
ኪሊያን ምባፔ በ2024/25 የውድድር ዓመት 31 ግቦችን በማስቆጠር የስፔን ላሊጋ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
ተጫዋቹ በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የወርቅ ጫማውን በማሸነፉ…