Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሌዋንዶውስኪ ከኤልክላሲኮ ጨዋታ ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከኤልክላሲኮ ጨዋታ ውጪ ሆኗል፡፡ የ37 ዓመቱ የባርሴሎናው የፊት መስመር ተጫዋች የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ነው የተገለጸው፡፡ ሌዋንዶውስኪ ባጋጠመው ጉዳት ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት ከሜዳው ሊርቅ እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል፡፡ በ10ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ መርሐ ግብር ባርሴሎና ወደ ሳንቲያጎ ቤርናባው በመጓዝ ከሪያል ማድሪድ ጋር ተጠባቂውን ጨዋታ ያደርጋል፡፡ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube…
Read More...

በቺካጎ ማራቶን ሃዊ ፈይሳ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ47ኛው የቺካጎ ማራቶን አትሌት ሀዊ ፈይሳ አሸንፋለች፡፡ አትሌት ሀዊ ፈይሳ ርቀቱን 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት መገርቱ አለሙ ደግሞ 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ሲቲ ካፕ "ሕዳሴ ዋንጫ" ቅዱስ ጊዮርጊስ መቻልን 2 ለ 1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል። የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች አሸናፊ ጌታቸው እና አዲሱ አቱላ አስቆጥረዋል። መቻልን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ቻርለስ ሙሴጌ ከመረብ አሳርፏል። መቻል፣ኢትዮዽያ ቡና እና ኢትዮ…

የአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች…

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ ለሚያስተናግዱት የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የአፍሪካ ሀገራት ማጣሪያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ይደረጋሉ፡፡ በማጣሪያው ምድቦቻቸውን እየመሩ የሚገኙት አራቱ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ እና አልጄሪያ ከወዲሁ የዓለም ዋንጫ ትኬታቸውን ቆርጠዋል፡፡…

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሜዳ ለውጥ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ሊደረጉ የነበሩ የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታዎች የሜዳ ለውጥ ተደርጎባቸዋል አለ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር፡፡ የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዘጠኝ ሳምንታት ውድድር በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ እንደሚደረግ ተገልጾ እንደነበር ማህበሩ አስታውሷል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት…

የቦካ ጁኒየርስ አሰልጣኝ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርጀንቲናው ክለብ ቦካ ጁኒየርስ ዋና አሰልጣኝ ሚጉኤል ሩሶ በ69 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ በፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ የፕሮስቴት ካንሰር ታማሚ ሆነው የቆዩት አሰልጣኙ÷ ባለፉት ዓመታት ከሕመማቸው ጋር እየተጋሉ ሥራቸውን ሲያከናውኑ እንደነበር ክለቡ አስታውቋል፡፡ ሚጉኤል ሩሶ ላበረከቱት አስተዋጽኦ…

ሩበን አሞሪም በ3 ዓመታት ውስጥ ምርጥ አሰልጣኝነቱን ማሳየት አለበት – ሰር ጂም ራትክሊፍ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ ባለድርሻ የሆኑት ሰር ጂም ራትክሊፍ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ምርጥ አሰልጣኝነቱን ማሳየት አለበት አሉ፡፡ ሰር ጂም ራትክሊፍ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በማንቼስተር ዩናይትድ ቤት በቂ ጊዜ እንደሚሰጠው ገልጸው፤ ታላቅ አሰልጣኝ መሆኑን ለማረጋገጥ ሶስት ዓመታት ያስፈልጉታል…