የበጋ መስኖ ልማት ዘር ማስጀመሪያ ፕሮግራም ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ይፋዊ የዘር ማስጀመሪያ ፕሮግራም በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ተካሄደ፡፡
አገራችን ለስንዴ ግዥ የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስ ያለንን መሬት፣ ጉልበትና ሀብት በማቀናጀት ተግባራዊ ብናደርገው በሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚያስፈልገውን ስንዴ ምርት መተካት እንደሚቻል የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር መለስ መኮንን ገልጸዋል፡፡
ግብርና የምጣኔ ሀብት እድገት ብቻ ሳይሆን የዜጎች የገቢ ምንጭ ነው ያሉት ደግሞ የደቡብ ክልል የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ዑስማን ስሩር ናቸው፡፡
የተጀመረው የበጋ መስኖ ዘር ማስጀመሪያ ፕሮግራም ለዚሁ ማሳያ እንደሆነ ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!