Fana: At a Speed of Life!

“በቃ”ወይም #No More ዘመቻ ሰላማዊ ሰልፍ በጃፓን ቶኪዮ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “በቃ” ወይም ‘#No More’ ዘመቻ ሰላማዊ ሰልፍ በጃፓን ቶኪዮ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተካሄዷል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በጃፓን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የተሳተፉ ሲሆን÷አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች የምዕራቡ ዓለም አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫና እና ጣልቃ ገብነት ማውገዛቸው ታውቋል፡፡

አሜሪካ በአፍጋኒስታን፣ ሶሪያ፣ ሊቢያና ሌሎች አገራት የፈጸመችው ድርጊት በኢትዮጵያ እንዲደገም እኛ ኢትዮጵያውያን አንፈቅድም ሲሉ ሰልፈኞቹ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸው ተገልጿል።

የምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ የሚያሰራጩትን ሐሰተኛ ዘገባ እንዲያቆሙ ጥሪ መቅረቡንና ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ፈተና አሸንፋ ትሻገራለች የሚሉ ሀሳቦችን ያዘሉ መፈክሮችም በሰልፉ ላይ ተስተጋብተዋል።

የሰልፉ አስተባባሪዎች አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ጫና እና ጣልቃ ገብነት እንድታቆም የሚያሳስብ ደብዳቤ በቶኪዮ ለሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ማስገባታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.