ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ የተነሱ አሸባሪዎች እራሳቸው እየፈረሱ ይገኛሉ – ምሁራን
አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ የተነሱ አሸባሪዎች እራሳቸው እየፈረሱ እንደሚገኙ ምሁራን ተናገሩ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሰቲ የህዝብና መንግስት አስተዳደር ተመራማሪ ዶክተር መሀመድ አሊ እንዳሉት፥ ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በአጭር ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እየተመራ ሀገር የማዳን ተልእኮውን እያሳካ ነው፡፡
ድሉ አሸባሪውን ብቻ ሳይሆን ከጀርባው ሲያዙት የነበሩትን ሀያላን ሀገራት ያሸማቀቀ ነው ብለውታል ዶክተር መሀመድ አሊ።
አሸባሪ ቡድኑም በህዝቦች ትብብር እየፈረሰ ይገኛል ነው ያሉት ።
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር አቶ ሀይሉ ነጋ፥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው ጥምር የጸጥታ ሀይል አሸባሪው ቡድን ሀገር የማፍረስ ግቡን እንደያዘ እያደባዩት እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን ሀገሪቱን ለእጅ አዙር ጦርነት ጭምር አሳልፎ የሰጠ ለራሱ ጥቅም ህዝቡን ዋጋ እያስከፈለ ያለ አጥፊ ሀይል በመሆኑ ቡድኑ አሁን ተንኮታኩቷል ሲላላክላቸው የነበሩት ሀገራት ከካይሮ እስከ ዋሽንግተን ሀፍረትም ተከናንበዋል ነው ያሉት ።
ምሁራኑ በእያንዳንዱ ግንባር የተሰለፈው ህዝብም በአንድነቱ ጠንክሯል ያሉ ሲሆን፥ በቀጣይም የሽብር ቡድኑ ለሀገሪቱ ቀጣይ የሰላምና ብልጽግና ስጋት እስከማይሆንበት ድረስ መስራት ይገባል ብለዋል ።
በሃይለእየሱስ መኮንን
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!